1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቻይና/በአፍሪቃ የልማት እንቅስቃሴ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 8 1999

ቻይና ከአሜሪካ እና ከፈረንሳይ ቀጥሎ በአፍሪቃ ሰፊ የንግድ ግንኙነት ያላት አገር ናት

https://p.dw.com/p/E0dQ
የቻይና በአፍሪቃ የመንገድ ግንባታ
የቻይና በአፍሪቃ የመንገድ ግንባታምስል AP

የቻይና እና የአፍሪቃ የንግድ ግንኙነት እ.አ ከ 2000 እስከ 2005 አ.ም ባለዉ ግዜ ዉስጥ በአራት እጥፍ እድገት አሳይቷል። የቻይና-አፍሪቃ የኢኮኖሚ ግንኙነት በሚቀጥሉት አመታት ከፍተኛ እድገት እንደሚያሳይ ይጠበቃል። በዚህም ረገድ የቻይና ፍላጎት ቢያንስ በአራት አመት ዉስጥ የአፍሪቃ ዋንኛዋ የኢኮኖሚ ሸሪክ መሆን ነዉ። ታድያ ይህ የቻይና እቅድ ለአፍሪቃ ኢኮነሚ እድገት ተስፍ ነዉ ወይስ ለአዉሮፓዉ የአፍሪቃ ልማት ትብብር እድገት አደጋ ? ኮነራድ አደናወር የተባለዉ የረዴት ድርጅት፣ ዶቸ ቬለ እና ጉዳዩ የሚያሳስበዉ የአፍሪቃ ማህበር በዚህ እርእስ ላይ ባደረጉት ዉይይት ዙርያ Ute Schaeffer ዘግባለች።

በቅርቡ የወጣዉ የአለም ባንክ የጥናት ጹሁፍ፣ ቻይና እና ህንድ በአፍሪቃ ያላቸዉ የንግድ ልዉዉጥ ፍላጎት መጨመር በርግጥ አፍሪቃን በአለም አቀፍ ደረጃ፣ በገበያዉ መድረክ ላይ እንድትዋሃድ መንገድ ይከፍታል። ይህ አይነቱ ታዳጊ አገሮች መካከል የሚደረግ አዲስ አይነት የንግድ ግንኙነት እመርታን እንደሚያገኝ ነዉ። የአዉሮፓ በአፍሪቃ የልማት ትብብር መርሆ፣ በተለይ ዲሞክራሲ ያልሰፈነባቸዉና፣ መልካም አስተዳደር የማያራምዱ አገሮች፣ ለምሳሌ እንደ ዚንቧቤ እና ሱዳን ባሉ ላላ ያለ የልማት ትብብር ሲኖር፣ ቻይና ግን ባንጻሩ ከነዚህ አይነቶቹ አገሮች ግንኙነቷ የተጠናከረ ነዉ። በዚንቧቤ የመንግስት ተቀናቃኝ ፓርቲ አባል የሆኑት David Coltar አገራቸዉ ዲሞክራሲያዊ አገዛዝ ያልሰፈነበት በመሆኑ የአዉሮፓ አገራት እርዳታቸዉንም ሆነ የልማት ትብብራቸዉን በማቀባቸዉ የሙጋቤ መንግስት ፊቱን ወደ ቻይና መልሶአል።
«ባለፉት ስድስት አመታት ሮበርት ሙጋቤ ወደ ምስራቁ አለም የሚያተኩር ፖሊሲ የጀመሩ ይመስላል። በዚህም መካከል ቻይና በዚንቧቤ በሁሉም ረገድ ተቀዳሜ ያላት ተሻራኪ አገር ሆናለች ። እንደምናዉቀዉም ቻይና በዚንቧቤ ዉስጥ በተለይ በሃይል ማመንጫዎችዋና ባልዋት የምአድን ሃብቷ ላይ አተኩሮ እንዳላት ነዉ። ቻይና በአሁኑ ወቅት ወደ ዚንቧቤ በሳምንት ሶስት የበረራ መስመር አላት። የቻይናም ጨርቃ ጨርቅ እና የጫማ ምርት የዚንቧቤዉን ምርት እየተጋፉት እደሆነ በግልጽ እያየን ነዉ»
David Coltart በመቀጠል በቅርቡ ይላሉ ቻይና ለሙጋቤ መንግስት የግማሽ ሚሊያርድ ዶላር እርዳታ ሰጥታለች። ይህም ገንዘብ ለጦር አዉሮፕላን መግዣ እንደሚዉል በምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተገልጾአል። ዚንቧቤ እስከ ቅርብ ግዜ ከሰሃራ በታች ካሉት አገሮች መካከል ሁለተኛዋ በኢኮኖሚ ጠንካራ የምትባል አገር ነበረች። በከርሰ ምድራቸዉ ሃብት ያላቸዉ አገሮች ዉስጥ ከ 4 ሚሊዮን ህዝቦች በላይ በረሃብ ይሰቃያሉ። የቻይና በአፍሪቃ የምታካሂደዉ የንግድ ግንኙነት ፖለቲካም የሃይል ምንጭ ረሃብ እንደያዛት ያሳያል። በመጭዎቹም አመታት ቻይና አንድ አራተኛዉን የነዳጅ ፍጆታዋን ከአፍሪቃ ለማስገባት ነዉ። የቻይና አፍሪቃ የንግድ ፖለቲካ ተመራማሪ Xuewun Gu ቻይና በአፍሪቃ ስላላት ሁኔታ
«በአሁኑ ወቅት ቻይና የሃይል ምንጭ ኢንዱስትሪ በመካከለኛዉ ምስራቅ እና በፍርስ ባህረ ሰላጤ የነዳጅ ምርት ላይ ጥገኛ እንዳትሆን አፍሪቃ ቁልፉን ሚና ትጫወታለች። እስከ 1990ዎቹ አጋማሽ ቻይና 60%የጋዝ ፍጆታዋን ከመካከለኛዉ ምስራቅ ነበር የምታስገባዉ። አሁን ወቅት ግን ይህን ቁጥር በመቀነስ 37% አድርሳለች። ለቻይና ወሳኝነት ያለአለዉ 21% የጋዝ ምርት ከአንጎላ እና ከሱዳን እናስገባለን»
የቻይና ከአፍሪቃ ጋር የጀመረችዉ የንግድ እና የኢኮኖሚ ግንኙነትም ለአፍሪቃ ታሪካዊ እና ብቸኛ እድል ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ታሪካዊ እና ብቸኛ ሊሆን የሚችለዉ ቻይና አስካሁን በአፍሪቃ ያሳየችዉን የመአድን እና የጋዝ ረሃቧን አቁማ በትክክለኛ የንግድ ግንኙት ስትተካዉ ነዉ። ይህ ትክክለኛ የንግድ ግንኙነት ታድያ አፍሪቃን ሙሉ በሙሉ ወደአለም አቀፉ ንግድ ገበያ ያበቃታል።