1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቻይና-አፍሪቃ የኤኮኖሚ ግንኙነት

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 3 2005

ቻይና በአፍሪቃ ውስጥ የምታደርገው የኤኮኖሚና የንግድ መስፋፋት በተፋጠነ ሁኔታ እያደገ መሄዱን የቀጠለ ጉዳይ ነው። ቻይና በአፍሪቃ ውስጥ የምታደርገው የኤኮኖሚና የንግድ መስፋፋት በተፋጠነ ሁኔታ እያደገ መሄዱን የቀጠለ ጉዳይ ነው።

https://p.dw.com/p/16zvJ
ምስል Getty Images

የቻይናና የአፍሪቃ የንግድ ልውውጥ አንድ ዓመት ቀደም ሲል ከነበረው ዘንድሮ 25 በመቶ በማደግ ከሁለት መቶ ቢሊዮን ዶላር በላይ ሲዘልቅ በቤይጂንግ አባባል የቻይና መዋዕለ-ነዋይም በሰፊው ጨምሯል። ሕዝባዊት ቻይና በፊናንስና በበጀት ቀውስ ከተወጠረውና የኤኮኖሚ ዕድገቱ ካቆለቆለው ከምዕራቡ ዓለም ዞር በማለት አፍሪቃን የወደፊት ስልታዊ የንግድ ሸሪኳ ለማድረግ ቆርጣ የተነሳች ነው የሚመስለው። ቻይና ከአፍሪቃ ጋር የምታደርገው የንግድ ልውውጥ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ በእጥፍ በማደግ ከአሜሪካ ወይም ከአውሮፓ ካላት ሊበልጥ እንደሚችል መነገሩም አልቀረም። ለመሆኑ አፍሪቃ በአጠቃላይና በተናጠልም ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ባላቸው የኤኮኖሚና የንግድ ትብብር እስካሁን ምን ያህል ተጠቃሚ ለመሆን ችለዋል፤ የወደፊቱስ አዝማሚያ ምንድነው? በጉዳዩ በዚህ በጀርመን በቻይና ጥናትና በዓለምአቀፍ ግንኙነት በማስተርስ ዲግሪ የኮሎኝ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ የሆኑትንና በወቅቱ በቦን ዩኑቨርሲቲ በከፍተኛ ጥናት ላይ የሚገኙትን ባለሙያ አቶ አሌክሣንደር ደምሴን አነጋግረናል፤ ያድምጡ!

መሥፍን መኮንን

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ