1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቻይና እና የአፍሪቃ ግንኙነት

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 14 2004

ቻይና ለአፍሪቃ ሀገራት በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የሚከፈል ሀያ ቢልየን ዶላር ብድር እንደምትሰጥ አስታወቀች። ቻይና ይህን ያስታወቀችው በቤይዢንግ በተከፈተው የቻይናና የአፍሪቃ መድረክ ላይ ነበር።

https://p.dw.com/p/15cbP
Source News Feed: EMEA Picture Service ,Germany Picture Service China's President Hu Jintao delivers a speech during the opening ceremony of the Fifth Ministerial Conference of the Forum on China-Africa Cooperation (FOCAC) at the Great Hall of the People in Beijing, July 19, 2012. Hu on Thursday offered $20 billion in loans to African countries over the next three years, boosting a relationship that has been criticised by the West and given Beijing growing access to the resource-rich continent. REUTERS/Jason Lee (CHINA - Tags: POLITICS BUSINESS)
ምስል Reuters

አዲሱ ብድር መሠረተ ልማቱን ለማሻሻል፡ የግብርናውንና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለማሳደግ እና ለትናንሾቹ እና ለመካከለኞቹ የንግድ ዘርፎች እንደሚውል ፕሬዚደንቱ አስረድተዋል። የአውሮጳ ህብረት ቻይና በሰብዓዊ መብት ይዞታቸው ለሚወቀሱ እና መልካም አስተዳደር ለጎደላቸው አፍሪቃውያት ሀገራት ብድር የምትሰጥበትን አሰራር ይወቅሳል። አፍሪቃውያን እአአ በ 1950 ዓመታት ያካሄዱትን ፀረ ቅኝ አገዛዝ ትግል የደገፈችው  ቻይና በወቅቱ ዋነኛዋ የአፍሪቃ የንግድ አጋር ናት። በቻይናውያን መዘርዝሮች መሠረት የንግዱ መጠን ወደ 166 ቢልየን ዶላር ይደርሳል።

አርያም ተክሌ

መሥፍን መኮንን