1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የነጭ አሜሪካዊዉ ፖሊስ ወንጀል

ረቡዕ፣ መጋቢት 30 2007

ፖሊሱ የታሰረው ባለፈው ቅዳሜ የተፈፀመውን ግድያ የሚያሳይ ቪድዮ ትናንት በብዙሃን መገናኛ ከቀረበ በኋላ ነው ።

https://p.dw.com/p/1F4HP
USA Polizist erschießt Mann Videostill
ምስል Reuters

South Carolina በተባለው የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራዊ ክፍለ ሃገር ውስጥ በሚገኘው North Charleston ከተማ አንድ ነጭ የፖሊስ መኮንን በሽሽት ላይ የነበረ አንድ ጥቁር ላይ በተደጋጋሚ ተኩሶ በመግደል ተከሶ ከታሰረ በኋላ ለፍርድ ቀርቧል ። ፖሊሱ የታሰረው ባለፈው ቅዳሜ የተፈፀመውን ግድያ የሚያሳይ ቪድዮ ትናንት በብዙሃን መገናኛ ከቀረበ በኋላ ነው ። የትራፊክ ህግን ጥሰሃል ተብሎ የተጠረጠረዉን የ50 ዓመት ጎልምሳ ለህይወቱ አስጊ በመሆኑ እንደተኮሰበት ገዳዩ ፖሊስ ቢናገርም ሟች ምንም ዓይነት የጦር መሣሪያ እንዳልያዘ ነው የተነገረው ። የቅዳሜው ግድያ በዩናይትድ ስቴትስ ፖሊስ በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚወቀስበትን የዘረኝነት እርምጃ እንደገና የመነጋገሪያ ርዕስ አድርጎታል ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ዛሬ በሳውዝ ካሮላይና የተቃውሞ ሰልፍ ጠርተዋል ።

መክብብ ሸዋ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ