1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኒው ሃምሻየሩ ቅድመ እጩዎች ምርጫ ውጤት

ረቡዕ፣ የካቲት 2 2008

የዴሞክራቶቹ ፓርቲ ሌላኛዋ እጩ ተፎካካሪ ሂላሪ ክሊንተን ከተፎካካሪያቸው በርኒ ሳንደርስ በ22 በመቶ ያነሰ ድምጽ በማግኝት ተሸንፈዋል።

https://p.dw.com/p/1HsmD
USA Vorwahlen New Hampshire
ምስል picture-alliance/dpa/J. Lane

[No title]


ትናንት ምሽት በኒው ሃምሻየር ፌደራዊ ግዛት በተካሄደው የ2016 የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ተወዳዳሪዎች ቅድመ ምርጫ ከሪፐብሊካን ፓርቲ ቢሊየነሩ ዶናልድ ትራምፕ፣ ከዴሞክራቶቹ ፓርቲ በኩል ደግሞ የቬርሞንት ፌደራዊ ግዛት የህግ መወሰኛ ምክር ቤት እንደራሴ በርኒ ሳንደርስ አሸንፈዋል ። በሪፐብሊካን ፓርት የኦሃዮ ግዛት ሀገረ ገዥ ጆን ኬሲሽ የ16 በመቶ ድምጽ በማግኘት ሁለተኛ ሲሆኑ፣ ከጥቂት ቀናት በፊት በአዮዋ ግዛት በተደረገ ተመሳሳይ ምርጫ አሸናፊ የነበሩት ቴድ ክሩዝ በትናንትናው ምሽት 12 በመቶ የኒው ሀምሻየር መራጮችን ድምጽ በማግኘት ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
የዴሞክራቶቹ ፓርቲ ሌላኛዋ እጩ ተፎካካሪ ሂላሪ ክሊንተን ደግሞ ከተፎካካሪያቸው በርኒ ሳንደርስ በ22 በመቶ ያነሰ ድምጽ በማግኝት ተሸንፈዋል። ናትናኤል ወልዴ ከዋሽንግተን ዲሲ ዠርዝሩን ልኮልናል።
ናትናኤል ወልዴ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ