1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኔታ እና የቄስ ትምህርት ቤት

ሰኞ፣ ጥር 19 2000

በርካታ ኢትዮጽያዉያን በቄስ ትምህርት ቤት ወንበር ከመዘርጋቱ በፊት የኔታን ጉልበት ስመን እሳቸዉ ከሌሉ ወንበራቸዉን ተሳልመን ነዉ ሀ ፣ ሁ የቆጠርነዉ። ይህን ህግ ሳያከብር ወደ ቄስ ትምህርት ቤት መጥቶ ጨዋታ ያማረዉ ህጻን በመጀመርያ ይመከራል፣ ሁለተኛ ካልሰማ የገሰጻል በሶስተኛ ግን የኔታን ኩርኩም ወይ አለንጋ ይቀምሳል

https://p.dw.com/p/E0lq
የቆሉ ትምህርት ቤት
የቆሉ ትምህርት ቤትምስል UN Photo/Rick Bajornas
በቤተ ክህነታችን ትልቁ የትምህርት ጅማሪ ጉዞ እንዲህ አሃዱ ይልና ስርአት ማክበር ህግ ማክበር ከቄስ ትምህርት ቤት ይጀምራል። የኔታ! እንደ ጨረቃ ያድምቆ፣ እንደ ሰርዶ ያለምልሞዎ፣ እንደ ዋርካ ያስፋዎ! በየኔታ ጉሮሮ ጠጅ ይንርቆር በጠላታቸዉ ጉሮሮ አጥንት ይሰንቀር ይባላል፣ በዘልማድ የኔታ በእዉቀት የሚስተካከላቸዉ ስለሌለ ደብተራዉ ሁሉ ምቀኛቸዉ ነዉና። የዛሪዉ ጥንቅር ስለ ቄስ ተማሪ ቤት እና ስለ የኔታ በጥቂቱ ያስቃኛል መልካም ቆይታ