1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የኔዘርላንድስ ምርጫ

ረቡዕ፣ መጋቢት 6 2009

አንድ መቶ ሐምሳ መቀመጫዎች ላሉት ምክር ቤት የ28 የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩዎች እየተፎካከሩ ነዉ።

https://p.dw.com/p/2ZF7t
Niederlande Wahl, Reportage aus Utrecht | Wahllokal Bahnhof
ምስል DW/A. Lueg

(Q&A) Niederlande Wahl - MP3-Stereo

የሆላንድ ወይም ኔዘርላንድስ ሕዝብ የወደፊት የምክር ቤት እንደራሴዎቹን ለምረጥ ዛሬ ድምፁን ሲሰጥ ነዉ የዋለዉ።አንድ መቶ ሐምሳ መቀመጫዎች ላሉት ምክር ቤት የ28 የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩዎች እየተፎካከሩ ነዉ።ዛሬ ድምፅ ከመሰጠቱ በፊት የተሰባሰበ የሕዝብ አስተያየት እንዳመለከተዉ በሥልጣና ላይ ያለዉ የጠቅላይ ሚንስትር ማርክ ሩተ የመሐል ቀኝ ፓርቲ ከፍተኛ የሕዝብ ድምፅ ሳያገኝ አይቀርም።የአዉሮጳ ሕብረትን፤ ሥደተኞችንና ሙስሊሞችን የሚጠሉት የቀኝr ፅንፈኛዉ ፖለቲከኛ የጌርት ቪልደርስ ፓርቲ ሁለተኛ ደረጃ ይይዛል።የምርጫዉ ዉጤት ከዛሬ ማታ ጀምሮ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።ሥለ ምርጫዉ ሒደት የብራስልስ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሴን በሥልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ገበያዉ ንጉሴን

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ