1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኔፓድ ዕቅድ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 26 2009

ኔፓድ በአህጉሪቱ ያሉ አትራፊ ፕሮጀክቶች ለባለሀብቶች በቀላሉ የሚደርሱበት የመረጃ ቋት በቀጠናዎች የማቋቋም ሀሳቡንም ባለፈው ሳምንት ይፋ አድርጓል፡፡

https://p.dw.com/p/2hYph
Angola Prekäre Straßen von Lubango
ምስል DW/A. Vieira

የኔፓድ አዲስ ዕቅድ

ለአፍሪካ ልማት አዲስ አጋርነት (ኔፓድ) ክፍለ ዓለማዊ የልማት ዕቅዶች ማሰባሰቢያ ማዕከል እንዲቋቋም እየጣርኩ ነው አለ፡፡ ኔፓድ በክፍለ ዓለሙ ያሉ አትራፊ ፕሮጀክቶች ለባለሀብቶች በቀላሉ የሚደርሱበት የመረጃ ቋት በቀጠናዎች የማቋቋም ሀሳቡንም ባለፈው ሳምንት ይፋ አድርጓል፡፡ የመረጃ ቋት ዝግጅቱ ለመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ቅድሚያ ይሰጣልም ተብሏል፡፡ ተቋሙ ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ ለሶስት ዓመት የሚሆኑ አትራፊ ፕሮጀክቶችን የገመገመ ስብሰባ ባለፈው ሳምንት በኮትዲቯር አቢጃን አካሂዷል፡፡ የቶሮንቶው ዘጋቢያችን አክመል ነጋሽ የኔፓድ ዕቅድ ከኢትዮጵያ አንጻር እንዴት ይታያል ሲል ባለሙያ አነጋግሯል፡፡ 
አክመል ነጋሽ 
ተስፋለም ወልደየስ
አርያም ተክሌ