1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የንባብ ባህል በኢትዮጵያ

ዓርብ፣ ሐምሌ 29 2008

በሀገሪቱ የአንባቢ ቁጥር እና የንባብ ባህል ጥናት የሚያስፈልገዉ ቢሆንም ፤የመጻህፍት ዋጋ መናር እና የቤተመጻህፍት ቁጥር አነስተኛ መሆን በችግርነት ይጠቀሳሉ

https://p.dw.com/p/1JcPI
Bangladesch Dhaka Bishwo Shahitto Kendro Bibliothek
ምስል DW

የንባብ ባህል በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የንባብ ባህልን ለማዳበር አሁን አሁን በተበታተነ መልኩም ቢሆን ጥረቶች እየተደረጉ ነው ። በዚህ ረገድ ንባብ እና መጻህፍት ላይ ያተኮሩ አውደ ርዕዮች ይጠቀሳሉ ። ስለ ሀገር ልማት ሲታሰብ ከቁሳዊ ልማት ባሻገር ሰብዓዊ ልማት ዋናው ነው ። በዚህ ረገድ መጻህፍት እና ንባብ ትልቁን ሚና ይጫወታሉ። በሀገሪቱ የአንባቢ ቁጥር እና የንባብ ባህል ጥናት የሚያስፈልገዉ ቢሆንም ፤የመጻህፍት ዋጋ መናር እና የቤተመጻህፍት ቁጥር አነስተኛ መሆን በችግርነት ይጠቀሳሉ ።በመሆኑም ከግለሰብና ተቁማት የተበታተነ ጥረት በተጨማሪ ለንባብ ባህል መዳበር መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ ንባብን ትኩረት አድርገዉ የሚስሩ አካላት ትናግረዋል። የነዚህ ዐውደ ርዕዮች ፋይዳ ፣እንዲሁም የንባብ ባህልን ለማዳበር የሚደረጉ ጥረቶች እና ተግዳሮቶቹ የዛሬው የባህል መድረክ ትኩረት ነዉ።

ፀሐይ ጫኔ

ነጋሽ መሐመድ