1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአለም ደሀ አገሮች ቁጥር መጨመር

ረቡዕ፣ ግንቦት 3 2003

በዓለም ውስጥ እጅግ የደኸዩ አገሮች የሚለውን ትርጉም ብንመለከት፤ የአንድ አገር ነዋሪዎች የአማካይ ገቢያቸው በዓመት ከ 900 ዶላር በታች ያሉትን ይመለከታል

https://p.dw.com/p/RNLh
ድሕነት በአፍሪቃምስል DW

የአለም ደሀ የሚባሉት አገሮች ቁጥር መጨመር

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየአስር አመቱ፤ የአለም ደሀ አገሮችን አስመልክቶ ጉባኤ ይከፍታል። እስካሁን የተካሄዱት ጉባኤዎች ያመጡት ለውጥ ይሄ ነው የሚባል አይደለም። እኢአ 1971 በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መዘርዝር ላይ የሰፈሩት አገሮች አሁንም መዝገቡ ላይ እንደሰፈሩ ናቸው። እንደውም ቁጥራቸው እጥፍ ሆኗል። «ሄለ የፕስን» የዘገበችውን ልደት አበበ ታቀርበዋለች።

በዓለም ውስጥ እጅግ የደኸዩ አገሮች የሚለውን ትርጉም ብንመለከት፤ የአንድ አገር ነዋሪዎች የአማካይ ገቢያቸው በዓመት ከ 900 ዶላር በታች ያሉትን ይመለከታል። ከደሀም ደሀ የተባሉ አገሮች ረሀብና ችግር የቀን በቀን ኑሮዋቸው የሆኑ፤ የህክምናና የትምህርት ጣቢያዎች ያልተስፋፉባቸው፤ ባጭሩ የሌላ አገር እርዳታ የሚሹ ማለት ይቻላል። የቀድሞው የኔዘርላንድ የልማት ሚንስትርና የተባበሩት መንግስታት የሚሊኒየም ግብ መስራች ( EVELINE HERFKENS) ችግሩን ያስረዳሉ።

« ሀብታሞቹ አገሮች፤ ቃል ገቡ። ደግመው ደጋግመው ቃል ገቡ። የአውሮፓ ህብረት እስከ 2015 ድረስ ከጠቅላላው የአገር ውስጥ ገቢ፤ 0,7 ከመቶውን ለእድገት እርዳታ እንደሚያውል ገለፀ። እውነቱን ለመናገር በ2015 ይሄ የገንዘብ ቼክ የት እንደሚደርስ አይታወቅም። ቡድን 8 ፤ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር፤ ለሚሊንየም የልማት ግብ እንደሚሰጡ ተናግረው ነበር። ኋላ ግን ባለፈው አመት ቃል የገቡት ምን እንደሆነ እንኳን የረሱት ይመስል ድምፃቸው ጠፋ፤ ገንዘቡንም አላቀረቡም።»

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መዘርዝር ላይ የሰፈሩ አገሮች እንደየቅደም ተከተላቸው፤ የሚያስረልጋቸውን እርዳታ ለመመደብ ይረዳል። ሆኖም እኢአ በ1971 መዘርዝሩ ላይ ከሰፈሩ አገሮች የተላቀቁት 3 አገሮች ብቻ ናቸው። ቦትስዋና፤ ኬፕ ቨርዴ እና የማልዲቬን ተጫፋሪ ደሴቶች። በተረፈ ከደሀም ደሀ የተባሉት አገሮች ላይ የሰፈሩት 24 አገሮች ዛሬ 48 ደርሰዋል። ባለው ጥሩ ያልሆነ መሰረተ ልማት ችግርና በቂ ያልሆነ የትምህርት አቅርቦት የተነሳ እነዚህ አገሮች ከአለም አቀፉ ምርት ተጠቃሚ ሊሆኑ አልቻሉም እንደ ባለሙያዎቹ አገላለፅ። ( EVELINE HERFKENS) እንደሚሉትም ለደሀ አገሮች የተደረገው እርዳታ እንደውም ለእድገታቸው ጥሩ ሚና አልተጫወተም።

« ነገሩ ስለ ግብርና ልማት ብቻ አይደለም፤ ውጤታማ የሆኑ ስራ እንዴት መፍጠር እንደሚቻልንም ያካትታል። ልማትን ስኬታማ የሚያደርጉ፤ እንደ ኃይል ምንጭና መሰረተ ልማትን የመሳሰሉ ጉዳዮች። እኛ ግን በብዛት ትኩረት የሰጠነው፤ በማህበራዊ ኑሯቸው ላይ ጫና የተደረገባቸው ላይ ነው እንጂ፤ ልማት ሊፈጥር የሚችለው ላይ አይደለም። »

ለ4ኛ ጊዜ ኢስታንቡል በተከፈተው ጉባኤ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኃላፊ ባን ኪሙን የእነዚህ እጅጉን ደሀ የተባሉት አገሮችን ቁጥር ግማሹ መቀነስ እንዳለበት አሳስበዋል። ለዚህ ደግሞ የታቀደው ጊዜ 10 አመት ነው። ይሁንና ይህንን ስኬታማ ለማድረግ ጥሩ መሰረተ ልማት፤ ትምህርትና ታማኝ የህግ አሰራር አስፈላጊ መሆኑን ከ ጀርመን የወረት( የኢንቨስትመንትና) የልማት ማህበረሰብ፤ ሚስተር ቡሩኖ አስምረውበታል።« በተወሰኑ አገሮች አመቺ ሁኔታ ያልተፈጠረላቸው በርካታ ድርጅቶች ጀርመን ውስጥ ይገኛሉ። በተጠቀሰው ምክንያት ሳቢያ በእነዚያ አገሮች መስራት የማይፈልጉ!ስለሆነም፤ ከአለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር በመተባበር መንግስታቸው ትኩረት ሊሰጥበት የሚገባው ጉዳይ ይሆናል። ለራሱ የግል ይዞታ ኢኮኖሚና ለአለም አቀፉ ልማት መንገድ የሚያመቻችበት!»

እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች ለማሟላት፤ ታማኝ የሆኑ የለጋሽ አገሮች የልማት እርዳታ ያስፈልጋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢስታንቡል በከፈተው ጉባኤ ላይም ወደፊት ከለጋሽ አገሮች የሚሰጠው ገንዘብ፤ በርግጥ በተግባር ላይ መዋሉን እንደሚቆጣጠር ገልጸዋል።

Lidet Abebe

Negash Mohammed