1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአልሸባብ ዕርምጃ ና መዘዙ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 14 2002

በሶማሊያ በሰብዓዊ ዕርዳታ ተግባር ላይ የተሰማሩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች መንግስትን ከሚወጋው አልሸባብ ከተባለው ቡድን በኩል የሚደርስባቸው ጫና ስራቸውን በአግባቡ እንዳያከናውኑ ዕንቅፋት እንደሚሆንባቸው አንድ የሶማሊያ ጉዳይ አጥኚ አስታወቁ ።

https://p.dw.com/p/LCQC
ምስል Bettina Rühl

የግጭቶችን መንስኤ በማጥናት መፍትሄያቸውን የሚጠቁመው ክራይስ ግሩፕ የተባለው ዓለም ዓቀፍ ድርጅት ባልደረባ ኤሪክ ጆን ሆገን ዶርን ዛሬ ለዶይቼቬለ እንደተናገሩት አልሸባብ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ለግብረ ሰናይ ድርጅቶች ያስቀመጣቸው የአሰራር ደንቦች ለተረጂው ህዝብ መድረስ ያለበት ዕርዳታ እንዲቀንስ ማድረጉ አይቀርም ። እንደ ተንታኙ ችግሩን ለመፍታት የዕርዳታ ድርጅቶች ከሚመለከታቸው የየአካባቢው አስተዳዳሪዎች ጋር መደራደራቸው እንድ አማራጭ ሊሆን ይችላል ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ