1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካን ምክር ቤት የCIA ምርመራ ዘገባ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 1 2007

የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ትናንት ይፋ ያደረገዉ የሀገሪቱ ማዕከላዊ የስለላ ተቋም CIA የምርመራ ስልቶች የሚዘረዝር ዘገባ ከተለያዩ ወገኖች ትችት እየተሰነዘረበት ነዉ።

https://p.dw.com/p/1E29h
Symbolbild CIA Saubermachen
ምስል picture-alliance/dpa

ዘገባዉ CIA በፕሬዝደንት ጆርጅ ቡሽ የስልጣን ዘመን የሽብር ተጠርጣሪዎችን ይመረምርበት የነበረዉ ስልት አሰቃቂ እንደነበር ሆኖም ሀገሪቱን ከጎርጎሪዮሳዊዉ 2001ዓ,ም መስከረም ጥቃት ወዲህ ከአደጋ ነፃ ሊያደርግ ያልቻለ መሆኑን በዝርዝር አሳይቷል። ዘገባዉን መርምሮ ያቀረበዉ የምክር ቤቱ የስለላ ጉዳይ ተከታታይ ኮሚቴ እንዳመለከተዉ በርከት ያሉ የሽብር ተግባር ተጠርጣሪዎች ጭካኔ ተፈፅሞባቸዋል፤ የCIA ምስጢራዊ እስርቤቶችም ወደማሰቃያ ስፍራነት ተለዉጠዋል። የአዉሮጳ ኅብረት ዘገባዉ ጭካኔ የተሞላበትና ዉጤት አልባ የሆነዉን የCIAን የምርመራ ስልት ማጋለጡ መርሃግብሩ እንዳልተሳካ አሳይቷል ብሎታል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በበኩላቸዉ የCIAን የምርመራ ስልት አጥብቀዉ ተችተዋል። አንድ የተመድ ልዩ መርማሪ በበኩላቸዉ በቡሽ ዘመነ ስልጣን ድርጊቱ እንዲፈፀም የፈቀዱ ባለስልጣናት ክስ እንዲመሰረትባቸዉ ሃሳብ አቅርበዋል። ዘገባዉ የተለያዩ ወገኖችን ትችት ማስከተሉ እየታየነዉ እዚያዉ አሜሪካን ዉስጥስ መገናኛ ብዙሃንም ሆኑ ዜጎች ምን እያሉ ይሆን? ከዋሽንግተን ዲሲ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋን ቀደም ብዬ በስልክ ጠይቄዋለሁ፤

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ