1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካን ባለሥልጣን ጉብኝት 

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 6 2009

ስለ ማሊኖቭስኪ የኢትዮጵያ ጉብኝት የአሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ጉዳይ ቃል አቀባይ ማርዮን ዎልስ ለዶቼቬለ በኢሜል በሰጡት መልስ ሀገራቸው ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት በኢትዮጵያ እንዲከበር ተጽዕኖ ታደርጋለች ብለዋል።

https://p.dw.com/p/2UK7f
US-Außenministerium
ምስል AFP/Getty Images/J. Richards

Beri Wash.(US -Ethiopian Human rights Dialogue) - MP3-Stereo

አንድ ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ለመምከር ኢትዮጵያ ይገኛሉ። በዩናይትድ ስቴትስ የዴሞክራሲ የሰብዓዊ መብቶች እና የሥራ ጉዳይ ረዳት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቶም ማሊኖቭስኪ የሚመራ የልዑካን ቡድን በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ መንግሥት እና ከክልል መንግሥት ባለሥልጣናት ከሲቪክ ማህበረሰብ አባላት እና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር ለመነጋገር ትናንት ነው አዲስ አበባ የገባው። ስለ ማሊኖቭስኪ የኢትዮጵያ ጉብኝት የአሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ጉዳይ ቃል አቀባይ ማርዮን ዎልስ ለዶቼቬለ በኢሜል በሰጡት መልስ ሀገራቸው ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት በኢትዮጵያ እንዲከበር ተጽዕኖ ታደርጋለች ብለዋል። የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
መክብብ ሸዋ 
ኂሩት መለሰ 

ሸዋዬ ለገሰ