1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካን የገንዘብ ድጋፍ እና አፍሪቃ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 17 2009

አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣናቸዉን ሲልዙ ለአፍሪቃ የሚሰጠዉ ገንዘብ ሊቀንስ ስለሚችል ኢትዮጵያን ጨምሮ የአካባቢዉ ሃገራት ይጎዳሉ ተባለ።

https://p.dw.com/p/2Ut7P
Symbol Geldwäsche USA
ምስል Getty Images

MMT_Beri. Washington (US Aid to Africa to decline ) - MP3-Stereo

 

ትራምፕ በአቋማቸዉ ከቀጠሉ የአፍሪቃ ሃገራት በተለይም ኢትዮጵያ፣ ናይጀሪያ፣ ጋና፣ ኮት ዴቩዋር፤ ደቡብ አፍሪቃ፣ አንጎላ እና ሌሎችም ሃገራት በጣም ይጎዳሉ፣ የምጣኔ ሃብታቸዉም ለአደጋ ይጋለጣል። ለዶቼ ቬለ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡ አንድ የኤኮኖሚ ባለሙያ በተለይ ከአፍሪቃ ሃገራት ከፍተኛዉን የገንዘብ ድጋፍ የምታገኘዉ ኢትዮጵያ ተጎጂ እንደምትሆን አመልክተዋል። ሌሎቹ የአፍሪቃ ሃገራት ከፍተኛ የማዕድን ሽያጭ የሚያደርጉ ሲሆን ኢትዮጵያ ግን 3,5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር  በማግኘት በፀረ ሽብር ዘመቻዉ የበለጠ የአሜሪካን አጋር ብትሆንም የእርዳታዉ ቀጣይነት አይታያቸዉም ምሁሩ። መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።  

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ