የአሜሪካ ምርጫና ውጤቱ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 24 2003ማስታወቂያ
በአሜሪካ ትላንት ምርጫ ተካሂዷል። በዚህም የፕሬዝዳንት ኦባማ ተቀናቃኞች በለስ ቀንቶአቸዋል። ሪፐብሊካኖች የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጪያዎችን በአብላጫነት አሸንፈዋል። በሌላኛው የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ሪፐብሊካኖች የተወሰኑ መቀመጪያዎችን ቢያገኙም የበላይነቱ ግን አሁንም በዲሞክራቶቹ እንደተያዘ ነው። በዚህም መሰረት የምክር ቤት የሪፐብሊካኖቹ መሪ የሆኑት እንደራሴ ጆን ቤነር ዲሞክራቷ ናንሲ ፔሎሲ ይዘውት የነበረውን የምክር ቤት አፈጉባዔነት ይረከባሉ።
አበበ ፈለቀ
መሳይ መኮንን
ነጋሽ መሐመድ