1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካ ዕጩ ፕሬዝደንቶች ክርክር

ሐሙስ፣ ጥቅምት 10 2009

የዲሞክራቲክዋ ፓርቲ ዕጩ ሒላሪ ክሊንተንና የሪፐብሊካን ተቀናቃኛቸዉ ዶናልድ ትራምፕ ትናንት ላስቬጋስ ከተማ ያደረጉት ክርክር በዉጪ ጉዳይ መርሕ፤ በስደተኞች ይዞታ እና በምጣኔሐብት ዕቅድ ላይ ያተኮረ ነበር።

https://p.dw.com/p/2RUZd
USA | Ende der 3. Präsidentschaftsdebatte 2016 in Las Vegas
ምስል Getty Images/C. Somodevilla

(Beri.WDC) US-TV-Duell - MP3-Stereo

 

ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ከሁለት ሳምንታት በኋላ በሚደረገዉ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የሚፎካከሩት የተቀናቃኝ ፓርቲዎች ዕጩዎች ሰወሰተኛ እና የመጨረሻ የቴሌቪዥን ክርክር ትናንት ተደርጓል። የዲሞክራቲክዋ ፓርቲ ዕጩ ሒላሪ ክሊንተንና የሪፐብሊካን ተቀናቃኛቸዉ ዶናልድ ትራምፕ ትናንት ላስቬጋስ ከተማ ያደረጉት ክርክር በዉጪ ጉዳይ መርሕ፤ በስደተኞች ይዞታ እና በምጣኔ ሐብት ዕቅድ ላይ ያተኮረ ነበር። ትራምፕ ከብዙ ዓመታት በፊት ሴቶች በገንዘብና ዝና በቀላሉ ይማረካሉ ማለታቸዉ ከተጋለጠ ወዲሕ የደጋፊዎቻቸዉ ቁጥር እየቀነሰ ነዉ። የዋሽግተን ዲ ሲ ወኪላችን መክብብ ሸዋ የትናንቱን ክርክር ተከታትሎ የላከልን ዘገባ አለ።

 

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ