1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር የእስያ ጉብኝት

ሰኞ፣ የካቲት 9 2001

የአሜሪካ የዉጩ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን በእስያ የሚያደርጉትን ጉብኝት ዛሬ በጃፓን ጀምረዋል።

https://p.dw.com/p/GvQ7
ሂላሪ ሮድሃም ክሊንተን
ሂላሪ ሮድሃም ክሊንተንምስል AP
ክሊንተን በሩቅ ምስራቅ ቆይታቸዉ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ያደጉባት ኢንዶኔዢያን ጨምረዉ፤ ወደደቡብ ኮሪያና ቻይናም ጎራ ይላሉ። በጉብኝታቸዉ ወቅትም ትኩረት የሳበዉን የዓለም የምጣኔ ሃብት ቀዉስና ጥንቃቄ የሚሻዉን ከሰሜን ኮርያ ጋ የተገናኘዉን የደህንነት ጉዳይ እንደሚነጋገሩበት ይጠበቃል። አሳሳቢዉ የአየር ጠባይ ለዉጥም ትልቁ አጀንዳቸዉ ነዉ።