1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል 50ኛ አመት ምስረታ

ሰኞ፣ ግንቦት 22 2003

አለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተመሰረተበትን ሃምሳኛ አመት ባለፈዉ ስምንት ታስቦ ዉሎአል። ድርጅቱ ሃምሳኛ አመቱን በማስመልከት ከሁለት ሳምንት በፊት ባወጣዉ ዘገባዉ በአለም ዙርያ በበርካታ አገራት የሚፈጸመዉን የሰብአዊ መብት ጥሰት አጋልጦአል።

https://p.dw.com/p/RQiZ
የአምነስቲ 50ኛ አመት በጀርመን ታስቦ ዉሎአልምስል dapd

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በሃምሳ አመቱ እንቅስቃሴዉ በአለም ዙርያ በርካታ የፖለቲካ እስረኞችን ነጻ አዉጥቶአል። በጀርመን የሚገኝዉ የድርጅቱ ቢሮ እንዲሁ ከተለያዩ አገሮች ከአስር እና ከስቃይ ነጻ ያወጣቸዉ ግለሰቦች ጥቂቶቹ በጀርመን የሚኖሩ ሲሆን ለድርጅቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦን በማበርከት ላይ ናቸዉ።
በአለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት Amnesty International ስር ሶስት ሚሊዮን የድርጅቱ አባላት እና ደጋፊዎች ሰዎች ላይ በግፍ የሚደርሰዉን በደል፣ እስር እና ጭፍጨፋ ለማዳን እገዛ ያደርጋሉ። በአለፈዉ አመት ብቻ በአለም ዙርያ በደረሰ የሰብአዊ መብት ገፈፋ በመቶ ስድሳ ሰባት ጉዳዮች ላይ እስረኞችን ለማዳን እርምጃ ተወስዶአል። የዛሪ ሃምሳ አመት እ.አ 1961 አ.ም በአንድ እንግሊዛዊዉ ጠበቃ የተረሱ ህዝቦች በሚል ርእስ በወጣዉ የጋዜጣ ላይ ዘገባ ሰበብ የተጀመረዉ ይህ የእርዳታ ሰጭ ድርጅት፣ እ.አ 1961 አ.ም በአለም አቀፉ ደረጃ በግፍ በእስር የሚሰቃዩ ህዝቦችን ለማዳን እንቅስቃሴዉን የጀመረዉ። አለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በሃምሳ አመት ዋዜማዉ ይፋ ባደረገዉ አመታዊ ዘገባ በአለም ዙርያ በ 89 አገራት የመናገር መብት መገፈፉን፣ እስረኞች የሚገረፉና የሚንገላቱ መሆናቸዉን እንዲሁም በ 48 አገራት በሰላማዊ መንገድ ተቃዉሞን የሚያሰሙ ሰዎች እንደሚታሰሩና እንደሚንገላቱ ሲገልጽ፣ ኢትዮጽያን አስመልክቶ ባወጣዉ ዘገባዉ፣ የሰብአዊ መብት እየከፋ መሄዱ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጽያ የሰብአዊ መብትን የሚከታተለዉ ኢሰመጉ ከፍተኛ ጫና እንዳለበት አስታዉቆል። ድርጅቱ በኤርትራ ላይ ባወጣዉ ዘገባ ደግሞ መንግስት የነጻ ፕሪስን ማፈኑን ዘጌች የፈለጉትን ሃይማኖት መከተል እንደማይችሉ እና ወጣቱን በብሄራዊ ጦር በመመልመል ህዝብን ለችግር የዳረገ ስርአት ሲል አስቀምጦታል።

አዜብ ታደሰ
ሸዋዪ ለገሰ