1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአምዐቱን ግቦች በመንግስታቱ ድርጅት ጉባኤ

ረቡዕ፣ መስከረም 12 2003

65 ኛዉ የተ.መ.ድ ጉባኤ ዛሪ ሶስተኛ ቀኑን ይዞአል። የጉባኤዉ ዋንኛ የትኩረት ርእስ ደግሞ የአምዐቱን ግብ መገምገም ነዉ።

https://p.dw.com/p/PJWh
የአምዐቱን ግቦች በመንግስታቱ ድርጅት ጉባኤምስል AP

በዚህ ጉባኤ ላይ የአፍሪቃ አገራት መሪዎች ባቀረቡት ንግግር በበለጸጉት አገራት የተገቡት ቃሎች ብዙም ባለመፈጸማቸዉ የታቀደዉን ግብ በተጠቀሰዉ የግዜ ሰሌዳ ተፈጻሚ ማድረግ ሊከብድ ይችላል ሲሉ ገልጸዋል። በሌላ በኩል የተ.መ.ድ ዋና ጸሃፊ ፓን ጊ ሙን በተለይ የህጻናት እና የሴቶችን ጤና ለመጠበቅ 40 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ባቀረቡት እቅዳቸዉ ገልጸዋል። መሳይ መኮንን ስለሶስቱ ቀን ጉባኤ ሰብሰብ ያለ ዘገባ አጠናቅሮአል።

መሳይ መኮንን

ሂሩት መለሰ