1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአረንጓዴዎቹ ፓርቲና አፍሪቃ

ረቡዕ፣ ጥር 5 2002

ለተፈጥሮ ጥበቃ የሚሟገተው የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ በአውሮፓ በተለያዩ ሀገራት በተለያየ ስም የተመሰረተ ቢሆንም በሀገር ደረጃ ታዋቂነትን በማትረፍ የጀርመኑን የአረንጓዴዎች ፓርቲ የሚወዳደር የለም ። ይኽው ፓርቲ የዛሬ ሰላሳ ዓመት ሲመሰረት በጀርመን የፖለቲካ ሂደት ውስጥ የጎላ ሚና ይጫወታል ብለው የገመቱ ጥቂቶች ነበሩ ።

https://p.dw.com/p/LV6n
ምስል AP

ሆኖም ቀስ በቀስ አድማሱን ያሰፋው ይኽው ፓርቲ ከተቋቋመ ከ 18 ዓመት በኃላ ተጣማሪ መንግስት ለመሆን በቃ ። እ.ጎ.አ ከ1998 እስከ 2005 ዓም ድረስ ከሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ በጀርመንኛው ምህፃር ከSPD ጋር ተጣምሮ ጀርመንን መርቷል ።ፓርቲው በተፈጥሮ ጥበቃ ቋሚ ተከራካሪነቱ ፀንቶ በመቀጥሉ ሌሎች ፓርቲዎችም በፖለቲካ አጀንዳቸው ቢያንስ በፅንሰ ሀሳብ ደረጃ የአካባቢ ጉዳዮችን እንዲያካትቱ ግፊት አድርጓል ። ከአውሮፓ ውጭ ያለውን ሁኔታ ስንመለከት በተለይ በአፍሪቃ የአረንጓዴዎቹ ፖለቲካ የለም ወይም ያን ያህል ተሰሚነት የለውም ማለት ይቻላል ። በዚህ ክፍለ ዓለም ይህ ስራ የተተወው መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ነው ። ከነዚህም አንዱ ለተፈጥሮ ጥበቃ የሚሟገተው የግሪንፒስ ኢንተርናሽናል ሀላፊ ኩሚ ናዱ ናቸው ። በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የዶይቼቬለዋ ሳራ ቦምካፕሬ ካማራ ያቀረበችውን ዘገባ ትርጉም ይልማ ኃይለ ሚካኤል ያቀርብልናል ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል ፣ ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ