1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአረንጓዴዎች ፓርቲ የሰላሳ ዓመት ጉዞ

ሐሙስ፣ ጥር 6 2002

በጀርመን የማህበራዊ ፍትህን መጓደል የፆታ እኩልነትን አለመከበር የዓለም የጦር መሳሪያ እሽቅድምድምን እና የአካባቢ ብክለትን በዋነኝነት በመቃወም በንቅናቄ ደረጃ ነበር የተጀመረው ። እየዋለ ሲያድር ደግሞ ወደ ፓርቲ አደገ ና የዛሬ ሰላሳ ዓመት አረንጓዴ ንቅናቄ በሚል ስም ተቋቋመ ።

https://p.dw.com/p/LVsj

ለመጀመሪያው ጊዜ በተሳተበፈበት የህዝብ ዕንደራሴዎች ምርጫ 1.5 በመቶ ድምፅ ያሸነፈው ይኽው ፓርቲ በመጨረሻው የጀርመን አጠቃላይ የምክር ቤት ምርጫ 10 በመቶ በላይ ድምፅ አግኝቷል ፓርቲው ሲመሰረት አሁን ለሚገኝበት ደረጃ ይበቃል ብለው የገመቱ ጥቂቶች ነበሩ ከተመሰረተ ትናንት ሰላሳ ዓመት የሞላው የጀርመኑ የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ