1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሰድና የምዕራቡ ዓለም ትብብር

ረቡዕ፣ ነሐሴ 21 2006

እ ጎ አ በ 1910 ማለቂያ ገደማ በቱኒሲያ የተጀመረው የህዝብ የለውጥ ንቅናቄ ፣ በፀደይ ሶሪያ ላይ ሲደርስ ፣ ፕሬዚዳንት በሺር ኧል አሰድም ሳያከትምላቸው አይቀርም የሚል ግምት ነበረ። የቱኒሲያው ቤን ዓሊ አገር ለቀው ለመኮብለል ሲገደዱ፣

https://p.dw.com/p/1D2k2

የግብፁ ሙባረክ ከሥልጣን ሲወገዱ የሊቢያው ጋዳፊ ሲገደሉ፤ የሶሪያው በሺር ኧል አሰድ፣
በብዙ ሺ የሚቆጠር ሕዝብ አደባባይ እየወጣ ሥልጣን እንዲለቁ ቢያስጨንቃቸውም ንቅንቅ አላሉም። አሰድ ፣ ያኔ፣ ከ«እስላማውያን አሸባሪዎች» ተጠንቀቁ ፣ በማለት ደጋግመው ከመናገራቸውም ፣ በህዝባቸውም ላይ የጭካኔ ርምጃ መውሰዱን ነበረ የመረጡ።

Bashar al-Assad Vereidigung 16.07.2014
ምስል Reuters/Syria TV

የዓረቡ ዓለም የለውጥ ንቅናቄ በተጀመረ በ 3ኛው ዓመት ሶሪያ ውስጥ ከ 190,000 በላይ ህዝብ አልቆም ቢሆን፤ አሳደee ከአስላማዊ አሸባሪዎች ተጠንቀቁ ሲሉ ያኔ ያሰሙትን ማሳሰቢያ ገና አሁን ነው ምዕራቡ ዓለም የተገነዘበው። እስላማዊ መንግሥት እመሠርታለሁ ብሎ የተነሳው ንቅናቄ ከሶሪያ እስከ ኢራቅ ሰፊ ቦታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሲቆጣጠር ፣ በመንገዱ ያገኘውን ማንኛውንም ተቃዋሚ እየደመሰሰ ነው።የአክራሪ ሱኑዎች ንቅናቄ ፤ ከዓረቡ ዓለምና ከአውሮፓ ጭምር የተውጣጡ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ወዶ -ገብ ተዋጊዎች አሏቸው። በመጀመሪያ በሶሪያ አማጽያን ላይ የዘመቱበት ጊዜ ነበረ። ይህም የደማስቆ መንግሥት እንዲያንሠራራ ሳይበጅ አልቀረም። አሁን ግን IS በሚል ምሕጻር የታወቁት አማጽያን ፣የሶሪያን ወታደሮችም በመውጋት ላይ ናቸው።

ሁኔታው ከዚህ ደረጃ ላይ ከደረሰ ወዲህ ፣ ዩማይትድ ስቴትስ የአውሮፓው ሕብረትና በዛ ያሉ የዓረብ ሃገራት አዲስ የታወጀው የከሊፋ ግዛት ትልቅ ተግዳሮት እንደሆነባቸው በመግለጽ ላይ ናቸው። የአሰድ አባባልና አቋም እንዴት ይሆን የሚታየው! በበርሊን የሳይንስና ፖለቲካ ተቋም ባልደረባ ፣ እንዲሁም የሶሪያ ጉዳዮች ተመራማሪ ፔትራ ቤከር ---

ISIS Kämpfer in Syrien 30.06.2014
ምስል picture alliance/AP Photo

«የተከተሉት የፖለቲካ ስልት በአንድ በኩል ቀጣይነት የነበረውና ያለው መሆኑን ሳያረጋግጥ አልቀረም። ከመጀመሪያውም፣ ለዴሞክራሲና ሰብአዊ መብት የተቀጣጠለውን አብዮት የአክራሪ እስላማውያን ጂሃዲስቶች ንቅናቄ ነው በማለት ከማውገዛቸውም፤ አባባላቸው ይበልጥ እውን እንዲሆን የአብዮቱ ኃይሎች እክራሪዎች እንዲሆኑ ሳይገፋፏቸው አልቀሩም።»

ከሶሪያ መንግሥት ድብቅ ቁም ስቅል ማሳያ ርምጃ ይልቅ የእስላማውያኑ ንቅናቄ የኃይል ርምጃ ነው ጎልቶ የሚነገረውና በመገናኛ ብዙኀንም ይበልጥ የሚወሳው። አማጽያኑ ፤ በሰሜናዊው ሶሪያ በራካ ጠ/ጋዛት ታብካ ላይ የሚገኘውን ስልታዊ አቀማመጥ ያለውን የአየር ኃይል ምሽግ ሲቆጣጠሩ፣ያልጠበቁት ችግር ነው ያጋጠማቸው። ብዙ ተቃውሞ ያላቸው አሰድም ቢሆኑ ያን ያህል ያልጠበቁት ሁኔታ ነው የተከሠተው። ስልታዊ አቅዳቸው ተሳክቷል። በራሳቸው ሀገር እጅግ አስፈሪ ሆነው የታዩት አማጽያን፤ አሰድ በዓለም አቀፍ መድረክ የተገለሉበትን አጥር የሚያፈርስ አጋጣሚ ሳይፈጠርላቸው አልቀረም።

«እስካሁን ይከተሉት ከነበረው የፖለቲካ ስልት ጋር አያይዘው የሚጠቅም መርኅ የሚቀይሱበት ወቅት አሁን ነው። በፀረ ሽብር ትግል የምዕራባውያ መንግሥታት ተጓዳኝ መሆናቸውን ማሳመን ከቻሉ አሰድ፤ ለተጨማሪ ዓመታትም በሥልጣን ላይ ተደላድለው የሚቆዩበትን ጊዜ ይሆናል በአስተማማኝ ሁኔታ የሚያራዝሙት። »

ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋሊድ ኧል ሙዓሊም፤ ሶሪያ በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥም ሆነ በስልታዊነት ማዕከላዊነት ያላት ሀገር በመሆኗ ፣ ሽብሩን መቋቋም የሚፈልጉ ሃገራት ከአኛ ጋር ቢተባበሩ ነው የሚበጃቸው ሲሉ ማስገንዘባቸው የሚታወስ ነው።

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ