1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአስቸኳይ ጊዜ ታሳሪዎች ጉዳይ

Merga Yonas Bula
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 10 2009

መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ በኋላ ከ11,000 በላይ ሰዎች ማሰሩን አስታዉቋል። ከነዚህ እስረኞች መካከል በህግ ይጠየቃሉ የተባሉት ብቻ ሲቀሩ፤  ሌሎቹ «የተሃድሶ ስልጠና» የተሰጣቸዉ እንደሚለቀቁ የኮማንድ ፖስቱ ፅሕፈት ቤት ሐላፊ  አቶ ሲራጅ ፌጌሳ ባለፈዉ ቅዳሜ  በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታዉቀዋል።

https://p.dw.com/p/2UXmt
Äthiopien Anti-Regierungs-Protesten
ምስል REUTERS/T. Negeri

Prisoners fo SoE - MP3-Stereo

እንደ አቶ ሲራጅ በአምስቱም «የተሃድሶ ስልጣና ማዕከላት» የነበሩት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ እስረኞች  ረቡዕ እንደምለቀቁ አስታዉቀዋል።

በጦላይ ወታደራዊ ካምፕ ብዙ ጊዜ የመንግስት ባለስልጣናት» ስልጣና እንደሚወስዱ የሚናገሩት ስማቸዉን መጠቀሱን የማይፈልጉ የአዳማ ነዋሪ፣ ግን  በካምፑ ዉስጥ የሚደረገዉ «አሰቃቂ» ድርጊቶች መሆኑን ነግረዉኛል ሲሉ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።

አቶ ሲራጅ እንዳሉት ኮማንድ ፖስቱ በ»ሁከትና ብጥብጥ» ተሳትፈዋል የሚላቸዉን ሰዎች በሁለተኛ ዙር 12, 500 በላይ ሰዎችን በቁጥጥር ስር እንዲዉሉ ተደርገዋል።

የእስረኞቹን የሰባዊ መብት ይዞታ የሚመረምረዉ አጣሪ ቦርድ በበኩሉ ከአንድ ወር በፊት ምርመራ መጀመሩን ቢገልጥም የምርመራ ዉጤቱ እስካሁን ለህዝብ ይፋ አልተደረገም።

ሥለ እስረኞቹ ብዛት፤ ይፈታሉ ሥለመባሉ እና ሥለ አጣሪዉ  ቦርድ ርምጃ ምን አስተያየት አለዎት ብለንም በፌስቡክ ደህረገፃችን ላይ አወያይተን ነበር። «ትክክለኛውን ቁጥር ለማወቅ በ15 ያባዙት» ያሉ ሲኖሩ፣ ሌሎች ደግሞ «ዋናው ነገር ምናልባት ሰላም ከሆኑ መፈታታቸው ነው፣ አጣሪ ኮሚቴ የሚባለውን ተውት» ሲሉ አስተያየታቸውን አጋርተውናል።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ