1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ረቡዕ፣ ጥቅምት 16 2009

መስከረም 28, 2009 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተደንግጎ፤ ከጥቂት ቀናት በኋላ ሁለት አሳታምዎች፣ ማለትም የኢትዮ/ምህዳርና የሃበሻ ወግ የተሰኙ ጋዜጦች፣ የግል ማተሚያ ቤቶች አዋጁ እንዳናሳትም ተፅእኖ አሳድሮብናል በማለታቸዉ ኅትመት ማቆማቸዉን ባለፈዉ ሳምንት ዴቼ ቬሌ መዘገቡ ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/2RjqN
Politikjournal Addis Standard
ምስል Addis Standard

M M T/ Emergency Decalration Impact on Print Media - MP3-Stereo

በተመሳሳይ አዲስ ስታንዳርድ የተሰኘዉ ወርኃዊ የእንግሊዝኛ መጽሔት፣ በዚሁ ምክንያት ሕትመቱን ለማገድ መገደዱን በትላንትናዉ ዕለት ማሳወቁን ዘግበናል።የኢትዮ/ምህዳር ዋና አዘጋጅ የሆኑት አቶ ጌታቸዉ ወርቁ ይህን ችግር ለመፍታት ወደ መንግስት ኮሙኒኬሼን ጽሕፈት ቤት እና የፍትህ ሚኒስቴር ሄደዉ አቤቱታ ቢያቀርቡም ምንም መፍትሄ
እንዳላገኙ ይናገራሉ። ወደኢትዮጵያ አሳታሚዎች ማኅበርም ይህኑ አቤቱታችን ወስደን ነበር ይላሉ አቶ ጌታቸዉ።

ይህንን ለማጠራትና የበለጠ መረጃ ለመማግኘት ከመንግሥትም ሆነ ከአሳታሚዎች ማኅበር በኩል ያደረግነዉ ሙከራ ሳይሳካልን ቀርቷል። አዋጁ ሌሎች ሀገሪቱ ዉስጥ ያሉት የንግድም ሆነ የፖለቲካ የኅትመት ዉጤቶች ላይ፣ በተለይም ሃሳብን በነፃ ማንሸራሸር ላይ ምን ተፅዕኖ ይኖረዋል ብለን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጤኝነትና ኮሙኒኬሼን ትምህርት ዘርፍ ዲን የሆኑት ዶክተር አብዲሳ ዜራይን አነጋግረን ነበር። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲደነገግ የሲቪልና የዴሞክራሲ መብቶችን ያቅባል የሚሉት ዶክተር አብዲሳ ይህም «እንደፈለጉ የመጻፍ፣ የመተቸትና አማራጭ ሃሳብ ማቅርብን ይገድባል» ይላሉ። 

ከ1997 ምርጫ በኋላ በኢትዮጵያ በተለያዩ ሁኔታዎች የፕሬስ ዉጤቶች ችግር ዉስጥ የገቡበት ምህዳር እንዳለ የሚናገሩት ዶክተር አብዲሳ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ግን አባብሶታል ይላሉ።

የፌስቡክ ተከታታዮቻችንን አዋጁ በኅትመት ዉጤቶች ላይ ስላስከተለዉ ተፅዕኖ አስተያየታችሁን እንዲያጋሩን ጠይቀን፤ አንዳንዶች «የግል ኅትመቶች ኃላፊነት የጎደላቸው ናቸው፣ ለ 25 ዓመታት ጥላቻን ነው የሰበኩን የፈጠራ ወሬ ነው የመገቡን» ሲሉ፣ ሌሎች ደግሞ «ምን ያልተዘጋ ነገር አለ፣ ሀገራችን ሁሉ ነገር የተበላሸ ነው ሀገራችን ወዴየት እንደምታመራ እንጃ ፈጣሪ ይወቅ» የሚሉ አስተያየቶችን ሰንዝረዋል። «እባካችሁ እንኑርበት፤» ያሉንም አሉ። 

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሰ