1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሥጋት

ሰኞ፣ ጥቅምት 7 2009

የኢትዮጵያ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና የአዋጁ አተገባበር መመሪያ በቋፍ ላይ የነበረውን የሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አያያዝ የደፈጠጠ ነው ሲሉ የተቃዋሚ ፖለቲከኞች ወቀሱ።

https://p.dw.com/p/2RLmX
Äthiopien Tote bei Anti-Regierungs-Protesten in Bishoftu
ምስል DW/Y. Gegziabher

Oponent partis reaction on state of emergency - MP3-Stereo

 ባለፈው ቅዳሜ ይፋ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መመሪያ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የቀይ ዞን በመመስረት የሰዓት እላፊ ገደብ ጥሏል። ማስፈጸሚያ መመሪያውን አስመልክቶ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒሥትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ እንደገለጡት «በአገሪቱ በሁሉም አቅጣጫዎች ባሉ ድንበሮች 50 ኪ.ሜ. ወደ ውስጥ ገባ ብሎ» የሚገኙ አካባቢዎች፤ ከአዲስ አበባ ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች በሚያመሩ ዘጠኝ መንገዶች ግራና ቀኝ በ25 ኪ.ሜትር ርቀት የቀይ ዞን መመሥረቱን አስታውቀዋል። በቀይ ዞን ውስጥ ከተካተቱት መካከል «የኢኮኖሚ አውታሮች፣ መሰረት ልማትና የኢንቨስትመንት ተቋማት፣ የእርሻ ልማቶች፣ ፋብሪካዎች» ይገኙበታል። መመሪያው በእነዚህ አካባቢዎች ከተፈቀደለት ሰራተኛ በስተቀር ከቀኑ 12 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰአት ድረስ ማንኛውም ሌላ ሰው እንዳይንቀሳቀስ ከልክሏል።የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር ያነጋገራቸው የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት «ህግን አገናዝቦ ያልወጣ» ያሉት አዋጅ እንዲሻር ጥሪ አቅርበዋል። 
ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር
እሸቴ በቀለ
ሒሩት መለሰ

Oponent partis reaction on state of emergency - MP3-Stereo