የአስቸኳይ ግዜ አዋጁና የኦሮሚያው ተቃዉሞ | ኢትዮጵያ | DW | 19.07.2017

ኢትዮጵያ

የአስቸኳይ ግዜ አዋጁና የኦሮሚያው ተቃዉሞ

ለ10 ወር የዘለቀው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናቶች ይቀሩታል። የአዋጁን አፈፃፀም በበላይነት የሚከታተለዉ ብሔራዊ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙም ይታወቃል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:50

የቀን ገቢ የግምት ተመን

የኮማንድ ፖስቱ ሴክሬታሪያት አቶ ሲራጅ ፈጌሳ በትላንትናዉ እለት ለመንግሥት ሚድያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ «የአዋጁ መራዘም ወይም መንሳትን ጉዳይ የሚመለከተው አካል ውሳኔ ይሆናል» ሲሉ ጠቅሰዋል። አቶ ሲራጅ ለላፉት ወራቶች ሲተገበር የነበረዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአገሪቱ «ሠላም እና ፀጥታ» መማምጣት ችለዋልም ብለዋል።

መንግስት በቅርቡ የቀን ገቢ የግምት ተመን ሥራ ላይ ማዋል ከጀመረ በኋላ በኦሮሚያ ክልል በአምቦ፣ በወሊሶ፣ በፊቼ እንድሁም በሌሎች ከተሞች የትራንስፖርትና የንግድ አገልግሎት መቋረጡን ለመረዳት ተችለዋል። አምቦና ወሊሶ የነበረዉ የንግድና የትራንስፖርት አድማ ዛሬ ቀን ላይ በከፊል በነቀምት እና በቡራዩ የንግድ ተቋማትን በመዝጋት ተቃዉሞ የማሰማት አዝማሚያዎች ታይተዋል ሲሉ ኦሮሚያ መስተዳድር የመንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳይ ኃላፊ አቶ አዲሱ ገልፀዉልናል።

የፖለቲካ ተንተኞችም ሆኑ አስተያየት ሰጭዎች አሁን በኦሮሚያ በግብር ጉዳይ ላይ የተነሳዉ ቅራኔና ወደ ተለየያዩ ከተሞች እየተስፋፋ ይገኛል የተባለዉ ተቃዉሞ የአዋጁን «ሠላምና ፀጥታ» ማስጠበቅ ሁኔታ ዋጋ እንዳሳጣ ነዉ የሚገልፁት። መንግስት በዚህ አኳኋን አዋጁንም ለማንሳት እንደሚቸገርም ይናገራሉ።

ትዉልድና እድገታቸዉ በምዕራብ ወለጋ ናጆ ከተማ እንደሆን ወልድ የሚምናገሩት ግን ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የጠየቁን ግለሰብ በቅርቡ በኦሮሚያ የተከሰተዉ ከፈተኛ ተቃዉሞን ተከትሎ ደንነቶች ሊይዙኝ ስሞክሩ ወደ ምስራቅ ሸዋ፤ ባቱ ከተማ እንደሄዱና እንደተሸሸጉ ተናግረዋል። በባቱ ከተማ ብዙ ሱቁች መዘጋታቸዉንና የማህበረሰቡ ብሶት ከግብር ዉጭ እንደሆነም ጠቅሰዋል። የባቱ ነዋሪዉ: «ከዝንብ ማር አይጠበቅም። ከዝንብ የምጠበቀዉ በሽታና ችግርን ነዉ። ከዚህ መንግስትም የሚገኘዉ እንደዛ ነዉ። በዚህ ክልል ዉስጥ ያለዉ ማህበረሰብ ከመንግስት ምንም ነገር እየጠበቀ አይደለም። ተስፋዉን ጨርሰዋል። የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ጥሩ ዉጤት አስገኝተዋል የሚሉት ለራሳቸዉ እንጅ ለሕዝቡ አደገኛ አዋጅ ነዉ።»

በኦሮምያ የተቀሰቀሰዉ ቁጣ በግብር ምክንያት ይሁን እንጅ ማህበረሰቡ በፊት ጠይቆ የነበረዉን ጥያቄ መልስ እያሻ ነዉ ሲሉ ስማቸዉን ያልጠቀሱ ሌላ ግለሰብ በዋትስአፕ ቁጥራችን ላይ የድምፅ መልክት ልከዉልናል።

አሁን በኦሮሚያ ያለዉ ሁኔታ ቅሬታ የማቅረብ ጉዳይ እንጂ ከፀጥታ ጋር የተያያዘ አይደለም የሚሉት አቶ አዲሱ አረጋ  አዋጁን «ዋጋ የሚያሳጣ ጉዳይ አይደልም» ብለዋል። በአምቦ የንግድ ተሽከርካሪና የደኅነት ተሽከርካሪ ላይ የደረሰዉ ጥቃት እንዲሁም በወሊሶ የነበረዉ አለመረጋጋትን ጨምሮ ሌሎች ቦታዎች ያለዉ ተቃዉሞ አስቸካይ ግዜ አዋጁን አይፈታተንም ይላሉ።

በኦሮሚያ ያለዉ ሠላምና ፀጥታ በተሻሻለ ሁኔታ ላይ እንደምገኝ አቶ አዲሱ አረጋ ተናግረዋል። በተወሰኑ ቦታዎች የተከሰተዉን «መጠነኛ ክስተት» ወስዶ አዋጁ ይራዘማል አይራዘምም የሚል ድምዳሜ መዉሰድ ግን ያሳስታል ብለዋል። 

መርጋ ዮናስ 
አዜብ ታደሰ


 

Audios and videos on the topic

Albanian Shqip

Amharic አማርኛ

Arabic العربية

Bengali বাংলা

Bosnian B/H/S

Bulgarian Български

Chinese (Simplified) 简

Chinese (Traditional) 繁

Croatian Hrvatski

Dari دری

English English

French Français

German Deutsch

Greek Ελληνικά

Hausa Hausa

Hindi हिन्दी

Indonesian Bahasa Indonesia

Kiswahili Kiswahili

Macedonian Македонски

Pashto پښتو

Persian فارسی

Polish Polski

Portuguese Português para África

Portuguese Português do Brasil

Romanian Română

Russian Русский

Serbian Српски/Srpski

Spanish Español

Turkish Türkçe

Ukrainian Українська

Urdu اردو