1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሸባብ ክፍፍልና የአባላቱ መገደል

ዓርብ፣ መስከረም 3 2006

መሃመድ ኡመር እንደሚለው በአልሸባብ መካከል ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ ክፍፍል ተፈጥረዋል በክፍፍሉ ሳቢያ የጥቃት ኢላማ ከሆኑት መካከል አል አሜሪኪ ኣንዱ ሲሆኑ በጥቃቱ የኣህመድ መዶቤ እጅ እንዳለበት ግን በስፋት ይነገራል። አህመድ መዶቤ ከሶማሊ ላንድ እንዲያውም መሐመድ ኦመር እንደሚለው የኢትዮፕያ አካል ከሆነው የኦጋዴን አካባቢ የወጡ ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/19hNG
**FILE** In a Tuesday Nov. 4, 2008 file photo, Somali militia of Al-Shabab are seen during exercises at their military training camp outside Mogadishu. Islamic fighters now control most of southern and central Somalia, with the crucial exceptions of Mogadishu and Baidoa. Islamic fighters declared Thursday, Nov. 13, 2008, that they will use strict Muslim rules to bring their lawless Horn of Africa country back under control. (AP Photo, File)
የአሸባብ ታጣቂዎችምስል dapd



የሶማሊያዉ አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን የአሸባብ መሪዎችና ታጣቂዎች ተከፋፍለዉ እርስ በርስ መገደደላቸዉ ተዘገበ።የተለያዩ የዜና ምንጮች እንደዘገቡት የቡድኑ ታጣቂዎች እርስ በርስ በገጠሙት ዉጊያ የዉጪ ዜግነት ካላቸዉ የቡድኑ ተዋጊዎች እና መሪዎች ቢያንስ ሰወስቱ ተገድለዋል። ከተገደሉት አንዱ የዩናይትድ ስቴትስ ዜግነት ያለዉ እና አል አሜሪኪይ በሚል ቅፅል የሚታወቀዉ የቡድኑ የተዋጊዎች መሪ ይገኝበታል።ዩናይትድ ስቴትስ አሸባብ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚያደርገዉን ፕሮፓንጋንዳ ይመራ የነበረዉ አል-አሜሪኪን ለያዘ፥ ለገደለ ወይም ያለበትን ለጠቆመ አምስት ሚሊዮን ዶላር እንደምትሸልም ከዚሕ ቀደም አስታዉቃ ነበር።ከአል-አሜሪኪ ሌላ አንድ የብሪታንያ ዜግነት ያለዉ የፓኪስታን ተወላጅና ዜግነቱ ያልተጠቀሰ ሌላ ተዋጊ መገደሉም ተዘግቧል።ጀዓፈር ዓሊ አጭር ዘገባ አጠናቅሯል።

በአሜሪካ አላባማ ክ/ሀገር የተወለደው ኦመር ሀማሚ አል አሜሪኪ በሚል የግሃድ ስሙ ይበልጥ ይታወቃል የ29 ዓመቱ አል አሜሪኪ ወደ ሶማልያ ኣቅንቶ ኣልሸባብን የተቀላቀለው እ ጎ ኣ በ2006 ዓ ም ሲሆን በሶማሊያ አልሸባብን ተቀላቅለው ከሚንቀሳቀሱት እና ይበልጥ ከሚታወቁት መካካልም ነበር

ሓማሚ በእንግሊዝናው ዜማ እና የቪዲዮ ቅንብር እያዘጋገ የሶማሊያን መንግስት ለመጣል ወጣቱን በስፋት ከመቀስቀስ ኣንስቶ በጸረ አሜሪካ እንቅስቃሴ ውስጥም በስፋት ይጠቀሳል ከዚሁ የተነሳ አሜሪካ እሱን ላስያዘ ወይም ላስገደለ የ 5 ሚሊየን ዶላር ጉርሻ እንደምትሰጥአስታውቃም ነበር
ትላንት የተገደለው ግን በራሱ በአልሸባብ አንጃዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግችት መሆኑ ታውቀዋል
ከእርሱም ጋር ኣንድ የብሪታንያ ዜግነት ያለው የፓኪስታን ተወላጅን ጨምሮ ትላንት ሶስት ያህሉ ተገድለዋል ኦስማን አልብሪታኒ የፓኪስታን ሳይሆን የግብጽ ተወላጅ ነው የሚሉም ኣሉየትላንቱ ግጭት የተካሄደው በሞቃዲሾ የዶቼቤሌ ተባባሪ ዘጋቢ የሆነው መሃመድ ኦመር ሁሴይን እንደዘገበው በባየደዋ ከተማ አቅራቢያ ንውበባይ ክ/ሀገር ከቤይደቦ ከተማ ጥቂት ኪ ሜትሮች ወጣ ብላ በምትገነው እና ሐባል በርባር በምትባል ስፍራ ነው የተገደሉት ይህ የሆነው ትላንት ቀትር ላይ ነው ለማረጋገጥም እኔ እራሴ የአካባቢውንነዋሪዎች ኣነጋግሬያለሁ, እናም ይሄው አሜሪካዊ ዜግነት ያለው እና አል አሜሪኪ ተብሎ የሚታወቀው ሰው መገደሉን ኣረጋግጠውልናል ኣንድ ሌላ የብሪታኒያ ዜግነትያለው የፓኪስታን ተወላጅም ከተገደሉት መካከል ነው

ሁኔታው መሃመድ ኡመር እንደሚለው በአልሸባብ መካከል ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ ክፍፍል ተፈጥረዋል በክፍፍሉ ሳቢያ የጥቃት ኢላማ ከሆኑት መካከል አል አሜሪኪ ኣንዱ ሲሆኑ በጥቃቱ የኣህመድ መዶቤ እጅ እንዳለበት ግን በስፋት ይነገራል አህመድ መዶቤ ከሶማሊ ላንድ እንዲያውም መሐመድ ኦመር እንደሚለው የኢትዮፕያ አካል ከሆነው የኦጋዴን አካባቢ የወጣ እና በኣሁኑ ጊዜ የአልሸባብ መሪዎችን በማደን ይታወቃል



ከሶማሊ ላንድ የሆነው ኣህመድ መዶቤ አጠቃላይ የኣልሸባብ መሪዎችን ለመግደል ቆርጦ እየተንቀሳቀሰ ይገናል ነገር ግን አልሸባብ ኣሁን የአካባቢውን ኣንዳንድ ቦታዎች ይቆጣጠራል ለምሳሌ ዲንሶር እና ባርዴር የተባሉትን አካባቢዎች ይቆጣጠራል ትክክለና ቁጥር መጥቀሱ ቢያስቸግርም ኣሁን በተጠቀሰው አካባቢ ደግሞ ሰላሳ ያህል የውጪ ጂሃዲስቶች ከኣልሸባብ ጋር እንደሚንቀሳቀሱ እገምታለሁ

በዘጋባዎች መሰረት አልሸባብ ከኪስማዮ በስተቀር የአካባቢውን ደቡብ ምእራባዊ አካባቢዎችም ይቆጣጠራል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኪስማዮ ማለትም የታችናው ጁባ ክ/ሀገር ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት አህመድ መዶቤ እራሳቸው ትላንትከሞቃድሾ ሲመለሱ ከተቃጣባቸው ጥቃት የተረፉት ለጥቂት ነበር በጥቃቱም መዶቤ በጠና የቆሰሉ ሲሆን ከእሳቸው ጋር ከነበሩት ልኡካን መካከል ስምንቱ ሞተዋል ሃያ ያህል ኣጃቢ ወታደሮችም መገደላቸው ታውቀዋል

የመዶቤ ኣነሳስም በኬንኃ ወታደሮች ታግዞ ከዚሁ አካባቢ ሲሆን ወታደራዊ ቲብብር ሊባል ባይችልም መዶቤ ከኢትዮፕያ ወታደራዊ ኃይል ጋርም ፓለቲካዊ ስምምነት እንዳለው ይነገርለታልመዶቤ ይላሉ ታዛቢዎች ፍላጎቱ የኣልሸባብን መሪዎች ጠራርጎ በማጥፋት ብቻውን ሞቃዲሾ መድረስ ነውለዚህ ደግሞ ኬንያም ሆነች ኢቲዮፕያ ይደግፉታልበኣሁኑ ጊዜ የኢትኆፕያ ወታደሮች ከባይደዋ መውጣታቸው ቢሰማም ዶሎ እና ሉቅ በተባሉ አካባቢዎች ይገናሉ ተብለዋል

epa03630386 A firefigther tries to put out smoldering vehicle at the scene of a suicide car bomb explosion near the presidential palace in Mogadishu, Somalia, 18 March 2013. Reports state at least 7 to 10 people were killed in the worst attack in Mogadishu this year. Somalia's Al Qaeda-linked Islamist militant group al-Shabab said that it had carried out the attack in an attempt to kill the Mogadishu security chief Khalif Ahmed Ilig. EPA/ELYAS AHMED
ምስል picture-alliance/dpa
epa03371186 (FILE) A file photograph showing Aboud Rogo Mohammed (L), talking with supporters in a Nairobi Kenya courtroom on 08 July 2003. Reports state on 27 August 2012 that Kenyan radical Islamist cleric, Aboud Rogo Mohammed, has been shot dead in a driveby shooting in Mombasa, kenya on 27 August 2012. The cleric was on US and UN sanction lists for allegedly supporting Somalia's al-Shabab militants. EPA/STEPHEN MORRISON +++(c) dpa - Bildfunk+++
አብድ ሮጎ መሐመድ-ከአሸባብ መሪዎች አንዱምስል picture-alliance/dpa

ጅዓፈር ዓሊ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ