1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሸባብ ጥቃት ስጋት በመቅዲሾ

ረቡዕ፣ መስከረም 24 2004

የሶማሊያ መዲና መቅዲሾ ነዋሪዎች ትናንት በአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት የሞቱትን ሰዎች ዛሬ ሲቀበሩ ውለዋል ።

https://p.dw.com/p/RpHq
ምስል picture alliance/dpa


የሶማሊያ የሽግግር መንግሥት ፕሬዝዳንት ሼክ ሸሪፍ ሼክ አህመድ በሶማሊያ የ3 ቀናት ሃዘን አውጀዋል ። ፕሬዝዳንቱ መዲናይቱን ወደፊት ሊያጋጥሙ ከሚችሉ የቦምብ ጥቃቶች ለመጠበቅ አስፈላጊው የፀጥታ ጥበቃ እርምጃ እንደሚወሰድም ቃል ገብተዋል ። ለትናንቱ ጥቃት ሃላፊነቱን የወሰደው አሸባብ ደግሞ ጥቃቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል ። ስለ መቅዲሾ ጊዜያዊ ሁኔታ ሂሩት መለሰ የየዶቼቬለ የመቅዲሾ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ሁሴን አዌይስ አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ