1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአባይ ወንዝ ፍትሀዊ አጠቃቀም ውዝግብ ና መፍትሄው

ረቡዕ፣ ሐምሌ 7 2002

አዲሱን የአባይ ወንዝ ፍትሀዊ አጠቃቀም ስምምነት የተቃወመችው ግብፅ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ፕሮጀክቶች ለመጀመር ያወጣቻቸውን ዕቅዶች በተፋሰሱ ሐገራት የትብብር ማዕቀፍ መሰረት እስከተከናወኑ ድረስ የወንዙ ፍሰት ላይ ችግር አያስከትልም ስትል በቅርቡ አስታውቃለች ።

https://p.dw.com/p/OJBq
ምስል picture-alliance / dpa

ይህን ያሳወቁት ባለፈው ሳምንት ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም መስፍን ጋር አዲስ አበባ ውስጥ የተነጋገሩት የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አቡል ጌት ናቸው ። በአባይ ተፋሰስ ሀገራት መካከል ከውሀው ፍትሀዊ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ በሚነሱት ችግሮች ላይ ለዶይቼቬለ አስተያየታቸውን የሰጡት ግብፅ የሚገኘው የአል አህራም ማህበራዊ እና ታሪካዊ ጥናቶች ማዕከል ሀላፊ ዶክተር ነቢል አብዱል ፈታህ ግብፅም ሆነች የተቀሩት የናይል ተፋሰስ አገራት ችግሩን ለመፍታት የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንደሚገባቸው ተናግረዋል ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ