1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአባይ ግድብ የግብፅ ተቃውሞና የኢትዮጵያ መልስ

ረቡዕ፣ ሰኔ 5 2005

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፉ የግድቡ አጥኚዎች ቡድን ያቀረበውን የጥናት ውጤት እንደገና የመከለስም ሆነ የግድቡን ሥራ የማስቆም ሃሳብ እንደሌላት ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።

https://p.dw.com/p/18oUY
ምስል DW/Azeb Tadesse Hahn

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የምትገነባውን ግድብ ማንም እንደማያስቆማት አስታወቀች ። የግብፅ መሪዎች በተደጋጋሚ የሚሰነዝሩት ዛቻም ትኩረቷን እንደማያስቀይርና በግድቡ ሥራ ላይም እንደማትደራደር አስታውቃለች ። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፉ የግድቡ አጥኚዎች ቡድን ያቀረበውን የጥናት ውጤት እንደገና የመከለስም ሆነ የግድቡን ሥራ የማስቆም ሃሳብ እንደሌላት ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። አምባሳደሩ የግብፅ ማስጠንቀቂያ ፣ በግብፅ ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ችግር ለማስቀየስ ታስቦ የሚደረግ ካልሆነ በስተቀር ለሁለቱም ሃገራት አይጠቅምም ብለዋል ። በሌላ በኩል ግብፅና ኢትዮጵያ በአባይ ውሃ የጋራ አጠቃቀም ሰበብ የገጠሙትን ውዝግብ በመነጋገር እንዲፈቱ የአፍሪቃ ህብረት ጠይቋል ። አምባሳደሩ ግን እስካሁን በዚህ በኩል ምንም የተጀመረ ነገር እንደሌለ አስታውቀዋል ። ያነጋገራቸው ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ