1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሞ ሕግ ባለሞያዎች ስብሰባ

ሰኞ፣ ኅዳር 5 2009

የዓለም አቀፉ የኦሮሞ ሕግ ባለሞያዎች ለሦስት ቀናት በዩኤዝ አሜሪካ አትላንታ ያካሄዱት ስብሰባ ትናንት እሁድ ተጠናቆአል። የሕግ ባለሞያዎቹ ስምንት ቦታ ተከፋፍለዉ ሲታገሉ የነበሩ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች ተዋኅደዉ በአንድነት እንዲታገሉ የሚያደርግ መሆኑ፤

https://p.dw.com/p/2ShT5
Äthiopien Proteste Gebet
ምስል Reuters/T. Negeri

mmt Ber. D.C (Exil-Vereinigung Oromor's - MP3-Stereo

 

እንዲሁም ኢትዮጵያ ዉስጥ ለፍትሕ፤ ለነጻነትና ለእኩልነት ከሚታገሉ ሌሎች ብሔረሰቦችም ጋር አብሮ ለመታገል መወሰኑን ወኪላችን መክብብ ሸዋ የላከልን ዘገባ ያሳያል። የዓለም አቀፉ የኦሮሞ ሕግ ባለሞያዎች ስብስብ  ረዘም ላሉ ጊዜያቶች አንድነት ለመፍጠር ዝግጅቶች ከተደረጉ በኋላ የመጀመርያዉ ጉባዔ ከ 15 ቀናት በፊት ለንደን ብሪታንያ ላይ አካሂዶ እንደነበር ይታወሳል። ዝርዝር ዘገባዉን የዋሽንግተኑ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ልኮልናል።   


መክብብ ሸዋ


አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ