1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አቶ ሐብተ ሥላሴ ታፈሰ

እሑድ፣ ነሐሴ 7 2009

የኢትዮጵያ የቱሪዝም አባት የሚባሉት እና ባለፈው ረቡዕ ነሐሴ 3 ቀን 2009 ዓም በ90 አመታተው ያረፉት የአቶ ሐብተ ሥላሴ የቀብር ስነ-ስርዓት ዛሬ ተፈጸመ።

https://p.dw.com/p/2i9XP
Äthiopien Trauerfeier Habte-Selassie Tafesse
ምስል DW/G.T. Haile Giorgis

አቶ ሐብተ ሥላሴ ታፈሰ

ብዙ ሀገር ጎብኚዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲጓዙ ትልቅ አስተዋፅዎ ያበረከቱት አቶ ሐብተ ሥላሴ ታፈሰ ዕሮብ ዕለት በ90 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የአቶ ሐብተ ሥላሴ የኢትዮጵያን «የ13 ወር ፀጋ» የሚለውን የቱሪዝም ማስተዋወቅያ የፈጠሩ እና ለኢትዮጵያ ቱሪዝም እድገት የለፉ ናቸው። ለሚደነቀው አስተዋጾዋቸውም የኢትዮጲያ ቱሪዝም አባት እየተባሉ ይጠራሉ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ በቀብር ስነ-ስርዓታቸው ላይ ተገንቶ አቶ ሐብተ ሥላሴ እንዴት እንደሚታወሱ ዘገባ አጠናቅሮ ልኮልናል። 

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ልደት አበበ