1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ መሪ የወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ መፈታት

ረቡዕ፣ መስከረም 26 2003

ትናንት ምሽት ጀምሮ እንደሚፈቱ ጭምጭምታ ሲሰማ ቆይቶ ዛሬ ረፋዱ ላይ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ መፈታታቸዉ ታዉቋል።

https://p.dw.com/p/PXNK
ምስል picture alliance/dpa

የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ወ/ት ብርቱካን ከእስር ተፈተዉ ቤታቸዉ ሊገቡ ሲሉ አግኝቶአቸዉ ነበር ዘገባ ልኮልናል፣ የህዝብ አስተያየትም አሰባስበናል።

በሌላ በኩል የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ስዬ አብርሃ የወ/ሪት ብርቱኳን መፈታት ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ተስፋ ነው ሲሉ ገልጸዋል። አቶ ስዬ ጨምረው እንደገለጹት የወ/ሪት ብርቱኳን ሚደቅሳ ከእስር መለቀቅ ለፓርቲያቸው ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮዽያውያን ትርጉም አለው። በቀጣይ ስለሚኖራት የፖለቲካ ተሳትፎ በእሷ ውሳኔ መሰረት የሚታወቅ መሆኑን አቶ ስዬ ጠቅሰዋል። የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ አባል አቶ ያዕቆብ ኃይለማርያም በበኩላቸው የወ/ሪት ብርቱኳን መፈታት ለዲሞክራሲ ለሚደረገው ትግል ጉልበት ይሰጠዋል ብለዋል። በጀርመን የኢትዮጵያውያን የሰብዓዊ መብቶች ኮሚቴ አባል ወ/ሮ አሳየሽ ታምሩ በወ/ሪት ብርቱኳን ሚደቅሳ ከእስር መለቀቅ የሚስደስት መሆኑን ጠቅሰው በኢትዮዽያ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እስኪፈቱ ድረስ ትግሉ ይቀጥላል ብለዋል። መሳይ መኮንን ዘገባ ይዟል።


ታደሰ እንግዳዉ፣ መሳይ መኮንን
አዜብ ታደሰ፣ አርያም ተክሌ