1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ መግለጫ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 8 2001

መሪው ወይዘሪት ቡርቱካን ሚዴቅሳ የታሰሩበት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከፓርቲው ህገ ደንብ ውጭ እየተንቀሳቀሱ ናቸው ያላቸውን ሀያ አንድ መስራችና ነባር የአመራር አባላቱን ማገዱን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል ።

https://p.dw.com/p/IqCh

ታደሰ ዕንግዳው ከአዲስ አበባ እንደዘገበው ከታገዱት አባላት ውስጥ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ዶከተር ሽመልስ ተክለ ፃዲቅና አቶ ወሮታው ዋሴ ይገኙበታል ። ዛሬ የታገዱት አባላት በበኩላቸው የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ በስልጣን ባልጓል ሲሉ ከሰዋል ።

ታደሰ እንግዳው ፣ ሂሩት መለሰ፣ሸዋዬ ለገሠ