1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአንድነት ለዴሞክራሲና ፍትሕ ፓርቲ መግለጫ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 29 2006

ለኢትዮጵያ አስተዳደር አማራጭ የፖለቲካ መርሕ ከቀየሱት በሰላማዊ መንገድ ከሚንቀሳቀሱት የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ ፣ አንድነት ለዴሞክራሲና ፍትሕ ፓርቲ ፤ በመጪው 2007 አዲስ ዓመት ፣ ሀገራዊ ኀላፊነትን መሸከም በሚያስችል መርኀ ግብር ለመሥራት

https://p.dw.com/p/1D6vL
ምስል DW

መዘጋጀቱን ገለጠ ። በገዥው ፓርቲ ተገፍቶ ካልወጣ በስተቀር አንድነት ለዴሞክራሲና ፍትሕ ፓርቲ በምርጫ እንደሚሳተፍ አስታውቋል። ፕሬዚዳንቱና የከፍተኛ አመራር አባላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤በፓርቲው ውስጥ በሐሳብ ልዩነት ሳቢያ ፤ የተወሰኑ የምክር ቤት አባላት ራሳቸውን ከኀላፊነት በማግለል በአባልነት ለመቀጠል የወሰኑበት ድርጊት ፤ ድርጅቱን የሚያጠናክር እንጂ የሚያዳክም አይደለም ማለታቸውም ተጠቅሷል።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ