1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ አባላት ያቀረቡት የጉባኤ ጥሪ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 7 2002

ከአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የተባረሩ መስራችና የአመራሩ የነበሩ አባላቱ መርህ ይከበር ዝም አንልም በሚል ከፓርቲዉ አመራር ጋር ዉዝግብ ዉስጥ ገብተዋል።

https://p.dw.com/p/MxCe
ምስል picture alliance/dpa

እነዚሁ ወገኖች ከጥቂት ጊዜ በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የፊታችን ቅዳሜ ሚያዝያ 10 ቀን 2002 ዓ.ም የጠቅላላ ጉባኤ እንደተጠራ አስታዉቀዋል። ጠቅላላ ጉባኤዉ እንዲጠራም 111 የጠቅላላ ጉባኤ አባላትን ማለትም የጉባኤዉ አንድ ሶስተኛ የይሁንታ ፊርማ ማሰባሰባቸዉን ገልጸዋል። ዝርዝሩን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ልኮልናል።

ታደሰ እንግዳዉ /አርያም ተክሌ