1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳዉ ህበርት በጋዛና የጋዝ ቀዉስ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 27 2001

የዘንድሮዉን የአዉሮጳያን ዓመት የ2009ኝን የስድስት ወራት የአዉሮጳ ህብረት የፕሬዝደንትነት ስልጣን የተረከበችዉ የቼክ ሪፑብሊክ በሩሲያና ዑክሬን መካከል በተከሰተዉ የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦት ዉዝግብ ሳቢያ በተከተለዉ ችግርና እስራኤል በጋዛ ሰርጥ እያካሄደች ባለችዉ ወታደራዊ ጥቃት ገና ከጅምሩ ተወጥራለች።

https://p.dw.com/p/GSUd
ዑክሬንን የሚያቋርጠዉ የጋዝ ቧምቧ
ዑክሬንን የሚያቋርጠዉ የጋዝ ቧምቧምስል AP

ሩሲያ የምዕራብ አዉሮጳ ዋነኛዋ ጋዝ አቅራቢ ስትሆን አብዛናዉ ጋዝዋ የሚያልፈዉ ዑክሬንን አቋርጦ በተዘረጋዉ ቧምቧ አማካኝነት ነዉ። ሞስኮ ከአዲሱ የአዉሮጳ ዓመት መባቻ አንስታ ለዑክሬን የምታቀርበዉን ጋዝ በዋጋ ባለመግባባትና በዉዝፍ እዳ መዘዝ አቋርጣለች። ሌሎችም በርምጃዉ ተነክተዋል።