1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ሕብረትና የቱርክ ዉል

ዓርብ፣ መጋቢት 9 2008

የሁለቱ ወገኖች መሪዎችን ስምምነት የመብት ተሟጋቾች እየተቃወሙት ነዉ።የአዉሮጳ ሕብረት ጦርነት፤ ሽብርና ጭቆናን ለሸሹ ስደተኞች ጥገኝነት መፈንጉን የተለያዩ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ነባር መርሁን የሚቃረን በማለት ተችተዉታል።

https://p.dw.com/p/1IG5D
Mark Rutte
ምስል picture-alliance/dpa/O.Hoslet

የአዉሮጳ ሕብረት እና የቱርክ ባለሥልጣናት «ሕገ-ወጥ» የሚሏቸዉ ሥደተኞች ወደ አዉሮጳ እንዳይገቡ ለማገድ ከዚሕ ቀደም የተስማሙበትን ሐሳብ ዛሬ በይፋ አፀደቁ።የሃያ ሥምምነቱ የሕብረቱ አባል ሐገራት መሪዎች እና የቱርኩ ጠቅላይ ሚንስትር አሕሜት ዳቩቶግሉ ማምሻቸዉ የደረሱበት ዉል ከመጪዉ ዕሁድ ጀምሮ ገቢራዊ ይሆናል።በሥምምነቱ መሠረት በቱርክ በኩል ወደ ግሪክ የገቡ ስደተኞች በሙ በግድ ወደ ቱርክ ይመለሳሉ።በተመለሱት ስደተኞች ቁጥር ልክ ቱርክ የሠፈሩ የሶሪያ ስደተኞች ወደ አዉሮጳ እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል።ሥለ ሌሎቹ ሐገራት ስደተኞች ዕጣ ፈንታ ግን ሥምምነቱ አይጠቅስም።

ቱርክ ለዚሕ ዉለታዋ በግዛቷ የሠፈሩ ስደተኞችን ለማስተናገድ ከአዉሮጳ ሕብረት ወደ 6 ቢሊዮን ዩሮ የሚዘጋ ገንዘብ ታገኛለች።የሕብረቱ አባል ለመሆን ከዚሕ ቀደም በየጊዜዉ እየተጀመረ የሚዳፈነዉ ድርድር ዳግም ይጀመራል።ከዚሕም በተጨማሪ የቱርክ ዜጎች ወደ ሸንገን አባል ሐገራት ያለ ቪዛ እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል።የሁለቱ ወገኖች መሪዎችን ስምምነት የመብት ተሟጋቾች እየተቃወሙት ነዉ።የአዉሮጳ ሕብረት ጦርነት፤ ሽብርና ጭቆናን ለሸሹ ስደተኞች ጥገኝነት መፈንጉን የተለያዩ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ነባር መርሁን የሚቃረን በማለት ተችተዉታል።

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ