1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ሕብረት ለኤርትራ የልማት ርዳታ ሊሰጥ ነዉ

ዓርብ፣ መስከረም 7 2008

የአዉሮጳ ሕብረት ለኤርትራ ከዚህ ቀደም ሊሰጥ አስቦ ይዞት የነበረዉን 200 ሚሊዮን ዩሮ የልማት ርዳታ ገንዘብ ሊሰጥ ማሰቡ ተመለከ። የሕብረቱ አባል ሃገራት እከያዝነዉ ዓመት መጨረሻ ለኤርትራ ስለሚሰጠዉ ስለዚህ የልማት ርዳታ ገንዘብ እንደሚወስኑ ይጠበቃል።

https://p.dw.com/p/1GYn7
Brüssel Europäische Kommission Außenansicht
ምስል picture-alliance/dpa/D. Kalker

[No title]


ገንዘቡ ለኤርትራ የሚሰጠዉ በተለይ ከኤርትራ በገፍ የሚፈልሱትን ስደተኞች ለመግታት እንደሆነ የኮሚሽኑ የልማትና ዓለማቀፍ ትብብር ኃላፊ ኔቨን ሚኒካ ትናንት ናይሮቢ ኬንያ በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል። ገንዘቡ በቀጥታ ሕዝቡ እጅ እንዲገባ እንደሚደረግም ባለስልጣኑ ተናግረዋል። የአዉሮጳ ሕብረት ፕሬዚዳንት ዦን ክሎድ ዩንከር ባለፈዉ ሳምንት ለሕብረቱ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር ካለፈው ዓመት ከጥር ወር አንስቶ እስካሁን 500 ሺህ ስደተኞች ወደ አዉሮጳ መግባታቸዉን ገልጠዋል። ከነዚህም አብዛኛዎቹ ከሶርያ ሊቢያና ኤርትራ ነው የመጡት። ዝርዝሩን ገበያዉ ንጉሴ አዘጋጅቶታል ።


ገበያዉ ንጉሴ

አዜብ ታደሰ
ሒሩት መለሰ