1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ሕብረት ርዳታ ለአፍሪቃ ቀንድ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 16 2009

ደቡብ ሱዳን 28 ሚሊዮን ዩሮ በማግኘት የመጀመሪያዉን ሥፍራ ስትይዝ፤ በርካታ ሕዝብ የተራበባት ኢትዮጵያ ሁለተኛዉን ከፍተኛ ርዳታ ታገኛለች።22,5 ሚሊዮን ዩሮ

https://p.dw.com/p/2Rjl6
Äthiopien Dürre
ምስል Getty Images/AFP/C. Cosier

(Beri.Brüssel) EU hilfe für Horn - MP3-Stereo

 የአዉሮጳ ሕብረት በድርቅ ለተጎዱ የአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ሐገራት ሕዝብ መርጃ 66.5 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚረዳ አስታወቀ።ሕብረቱ ትናንት እንዳስታወቀዉ ርዳታዉ  በርካታ ሕዝብ ለተራበባቸዉ ለኢትዮጵያ፤ለሶማሊያ፤ለደቡብ እና ለሰሜን ሱዳን የሚከፋፈል ነዉ።በሕብረቱ መግለጫ መሠረት ካጠቃላዩ ርዳታ በጦርነት የወደመችዉ ደቡብ ሱዳን 28 ሚሊዮን ዩሮ በማግኘት የመጀመሪያዉን ሥፍራ ስትይዝ፤ በርካታ ሕዝብ የተራበባት ኢትዮጵያ ሁለተኛዉን ከፍተኛ ርዳታ ታገኛለች።22,5 ሚሊዮን ዩሮ።ሶማሊያና ሰሜን ሱዳን እያንዳዳቸዉ 8 ሚሊዮን ዩሮ ያገኛሉ።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ  ተከታዩን  ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ