1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ሕብረት ዕቅዱን አፀደቀ

ዓርብ፣ ጳጉሜን 6 2007

የአዉሮጳ ሕብረት አባል መንግሥታት ሥደተኞችን በኮታ እንዲቀበሉ የሕብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝደንት ዦን ክሎድ ዩንከር ከትናንት በስቲያ ይፋ ያደረጉትን ዕቅድ የሕብረቱ ምክር ቤት በአብላጫ ድምፅ አፅድቆታል። አባል ሐገራት 160 ሺሕ ስደተኞችን ተከፋፍለዉ እንዲቀበሉ የሚለዉ ሐሳብ የዕቅዱ ዋና ነጥብ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1GVEi
ምስል picture-alliance/dpa/V. Fedorenko

[No title]

የጎርጎርያኑ 2015 ከተጀመረበት ካለፈዉ ጥር እስካሁን በተቆጠሩት ሰምት ወራት ከአስራ አንድ ቀናት ዉስጥ የሜድትራንያን ባሕር አቋርጦ አዉሮጳ የገባዉ ስደተኛ ቁጥር ከ432 ሺሕ መብለጡን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት IOM አስታወቀ። ሰወስት ሺሕ የሚሆኑ ባሕር ዉስጥ መሞታቸዉ ተዘግቧል። ሰሞኑን አዉሮጶችን በጣም ያሳሰበዉ፤ የሚያነጋግርና የሚያወዛግበዉ ግን በደቡብ-ምሥራቅ አዉሮጳ በኩል በገፍ የሚገባዉ ስደተኛ ነዉ። የአዉሮጳ ሕብረት አባል መንግሥታት ሥደተኞችን በኮታ እንዲቀበሉ የሕብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝደንት ዦን ክሎድ ዩንከር ከትናንት በስቲያ ይፋ ያደረጉትን ዕቅድ የሕብረቱ ምክር ቤት በአብላጫ ድምፅ አፅድቆታል። አባል ሐገራት 160 ሺሕ ስደተኞችን ተከፋፍለዉ እንዲቀበሉ የሚለዉ ሐሳብ የዕቅዱ ዋና ነጥብ ነዉ። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ አለዉ።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሠ