1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ምክር ቤትና ሥራ ላይ የሚገኙ አባላት

ረቡዕ፣ ግንቦት 19 2001

በ27ቱም የአዉሮጳ ኅብረት አባል አገራት የሚኖሩ 3 መቶ 37 ሚሊዮን አዉሮጳዉያን-የአዉሮጳ ፓርላማ ተወካዮቻቸዉን ለመምረጥ የቀራቸዉ ጊዜ ከአንድ ሳምንት ብዙም አይበልጥም።

https://p.dw.com/p/Hyck
ምስል AP

ይሁን እንጂ በዘንድሮዉ ምርጫ የኅብረተሰቡ ተሳትፎ የዛሬ አምስት ዓመት ከነበረዉ ያነሰ ሊሆን እንደሚችል የህዝብ አስተያየት መለኪያዎች እየጠቆሙ ነዉ። ይህም ለመምረጥ የሚወጣዉ ህዝብ ከሚጠበቀዉ በታች በጣም ወርዶ የፓርላማዉን ብሎም በአጠቃላይ የኅብረቱን ህጋዊነት ጥያዌ ዉስጥ እንዳይከተዉ ስጋት አጭሯል። ይህ በእንዲህ እንዳለም አንድ ድረ ገፅ የኅብረቱ ፓርላማ አባላት ባለፈዉ ዓመት በተመረጡበት ስራ ላይ የተገኙበትን ጊዜ ተከታትሎ በመመዝገብ ብቅ ብሏል።

ገበያዉ ንጉሤ/ ሸዋዬ ለገሠ/ተክሌ የኋላ