1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ኅብረት መሪዎች ጉባኤ

ዓርብ፣ ጥቅምት 15 2006

የአዉሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት መሪዎች ከትናንት ከቀትር በኋላ አንስቶ እስከዛሬ ያካሄዱትን የሁለት ቀናት ጉባኤ አጠናቀቁ።

https://p.dw.com/p/1A6N6
ምስል Reuters

ሆኖም ጉባኤዉ አስቀድሞ በያዛቸዉ የመነጋገሪያ ነጥቦች ላይ ከመነጋገር ይልቅ ትኩረቱ በጣልያኗ ደሴት ላምፔዱዛ አቅራቢያ ያለፈዉ የስደተኞች ህይወት እንዲሁም የአሜሪካን የስለላ ተቋም የአዉሮጳ መሪዎችን የስልክ ግንኙነት ሳይቀር ጠልፏል በሚለዉ መወሰዱ ነዉ የተገለጸዉ።

EU Gipfel Van Rompuy und Barroso Abschluss-PK 25.10.2013
ሄርማን ፋን ራምፖይ እና ሆሴ ማኑኤል ባሮሶምስል Georges Gobet/AFP/Getty Images

በዉሳኔያቸዉም የሜዲትራኒያን ባህርን እያቋረጡ ወደአዉሮጳ ለመግባት የሚሞክሩ ሕገ ወጥ ስደተኞችን የጫኑ ጀልባዎችን የመከታተል ርምጃ እንዲወሰድ ከሚለዉ አንስቶ ድንበር ጠባቂዎች ህይወት የማዳን ተግባር እንዲያከናዉኑ የሚለዉ ሲጠቀስ፤ ስለላዉን በሚመለከት ደግሞ መሪዎቹ የሁለትዮሽ ግንኙነትን እንደሚጎዳ በማመልከት ከዋሽንግተን ማብራሪያ ጠይቀዋል። ጉባኤዉ ሲጠናቀቅ የተካሄደዉን ጋዜጣዊ ጉባኤ የተከታተለዉ የብራስልሱ ወኪላች ገበያዉ ንጉሤን ስለጉዳዩ ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ አነጋግሬዋለሁ፤

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ