የአዉሮጳ ኅብረት የሁለት ቀን ጉባኤ
ሐሙስ፣ መጋቢት 3 2007ማስታወቂያ
የኅብረቱ ፕሬዝደንትነትን መንበር የያዘችዉ ላቲቪያ 28 አባላት ያሉት ኅብረት የድንበር አካባቢዎችን አጠናክሮ ለመጠበቅ እንዲያስችለዉ በቂ ገንዘብ እንዲመደብ እየጠየቀች ነዉ። ባለፈዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ብቻም ከሁለት መቶ ሺህ የሚበልጡ ጥገኝነት ጠያቂዎች በሕገወጥ መንገድ ወደተለያዩ የኅብረቱ ሃገራት መግባታቸዉ ተገልጿል። ስለሚኒስትሮቹ ጉባኤና መነጋገሪያ ነጥቦች ብራስልስ የሚገኘዉን ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ገበያዉ ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ