የአዉሮጳ የእግር ኳስ ግጥምያና ፈረንሳይ
ዓርብ፣ ሰኔ 3 2008ማስታወቂያ
ፓሪስ ከተማ ባለፈዉ ኅዳር ወር ላይ በአሸባሪ ጥቃት ከደረሰባት በኋላ ዛሬ የዓለም የእግር ኳስ አፍቃሪም ሆነ የብዙኃን መገናኛዎች ዓይናቸዉን ወደ ፓሪስ መልሰዋል። ፓሪስ ላይ የሚጀምረዉ የዘንድሮዉ ግጥምያ አዘጋጅዋ ፈረንሳይና ሮማንያ ይጋጠማሉ። እንደሚታወቀዉ ባለፈዉ ኅዳር ወር ፓሪስ ላይ በአሸባሪዎች ከፍተኛ ጥቃት፤ ከ100 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ከዚህ ሌላ ፓሪስ የስራ ማቆም አድማ፤ እንዲሁም ሌሎች በርካታ ማኅበራዊ ችግሮችን ተጋፍጣ ነዉ የሰነበተችዉ። ፈረንሳይ የአዉሮጳ የእግር ኳስ ዋንጫ ግጥምያን ስታስተናግድ ያሉባትን ችግሮች ቀርፋ ይሆን? የደሕንነቱ ጥበቃስ ምን ይመስላል? ፓሪስ ፈረንሳይ የምትገኘዉ ወኪላችንን በስልክ ጠይቀናታል።
ሃይማኖት ጥሩነህ
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ