1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ፓርላማ እና የኤርትራ ጉዳይ

ረቡዕ፣ መጋቢት 9 2007

የአዉሮጳ ፓርላማ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚቴ ትናንት በኤርትራ ጉዳይ ላይ ተወያየ። ኮሚቴዉ በዉይይቱ በኤርትራ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ያለዉን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የሕዝቡንም ችግር መርምሯል።

https://p.dw.com/p/1Esnn
Blick über die Häuser von Asmara, Independence Avenue
ምስል picture-alliance/ dpa

በአደገኛ ሁኔታ የሜድትራኒያንን ባሕር እያቋረጡ ወደአዉሮጳ ከሚገቡ ስደተኞች ዉስጥ ብዙዎቹ ኤርትራዉያን መሆናቸዉ የሚነገር ሲሆን ይህም በሀገሪቱ በሰፈነዉ አምባገነናዊ ሥርዓት አስገዳጅነት እንደሆነ ይገመታል። የአዉሮጳ ፓርላማ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚቴም ትናንት በኤርትራ ጉዳይ በጠራዉ ስብሰባ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የኤርትራ ጉዳይ ልዩ አጥኚ ሼይላ ኪታሩትና ቀድሞ በቤልጂየምና በአዉሮፓ ኅብረት የኤርትራ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር አንደብርሃን ወልደጊዮርጊስ ዋና ተናጋሪዎች ነበሩ። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሤ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ