1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ህብረት፡ ሞሳድ እና በሀማስ ባለስልጣን ግድያ የቀጠለው ክርክር

ማክሰኞ፣ የካቲት 16 2002

የአውሮጳ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች አንድ ከፍተኛ የሀማስ ባለስልጣን ከአንድ ወር በፊት በዱባይ የተገደሉበትን እና ገዳዮቹ ለዚሁ ተግባራቸው ማካሄጃ በተጭበረበሩ የአውሮጳ ህብረት ፓስፖርቶች የተጠቀሙበትን ድርጊት አወገዙ።

https://p.dw.com/p/M9JW
የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቪግዶር ሊበርማንምስል AP

በዚሁ ግድያ ዱባይ እስራኤልን ተጠያቂ ስትል ወቀሳ አሰምታለች። ይሁንና፡ በኢራን አቶም ፖሊሲ፡ በሄይቲ፡ በኒዠርና በዩክሬይን ጉዳዮችም ላይ ጭምር የመከሩት ግን ትልቁን ትኩረታቸውን በሀማስ ባለስልጣን ግድያ ላይ ያሳረፉት አውሮጳውያኑ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮቹ እስራኤልን ለግድያው በቀጥታ ተጠያቂ ከማድረግ ተቆጥበዋል።

ክርስቶፈር ሀስልባኽ/አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ