1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ህብረት እና የዩኤስ አሜሪካ የንግድ ግንኙነት

ሰኞ፣ የካቲት 2 2007

የአውሮጳ ህብረት እና ዩኤስ አሜሪካ በመካከላቸው ሊያቋቁሙት ያሰቡትን ነፃ የንግድ ቀጠናን የተመለከተውን ስምንተኛውን የድርድር ዙር በዚህ ሳምንት በብራስልስ በዝግ ስብሰባ አካሄዱ።

https://p.dw.com/p/1EYJt
Flaggen EU und USA Symbolbild TTIP
ምስል imago/C. Ohde

የአውሮጳ ህብረት እና ዩኤስ አሜሪካ ይቋቋማል የሚባለው በምሕፃሩ « ቲ ቲ አይ ፒ » የሚባለው የትራንስ አትላንቲክ የንግድ እና የኢንቬስትመንት አጋርነት በዓለም ትልቁ የንግድ ቀጠና ሊሆን እንደሚችል ይነገራል። ሁለቱ ፣ ማለትም፣ የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት እና ዩኤስ አሜሪካ ከዓለም ኤኮኖሚ መካከል በወቅቱ አንድ ሶስተኛውን ይሸፍናሉ። ውሉ በሚፈረምበትም ጊዜ በነዚህ ሀገራት የሚኖሩት ሰዎች የነፍስ ወከፍ ገቢ በአማካይ በዓመት በሶስት ከመቶ ከፍ እንደሚል ነው የሚገመተው። ውሉ ለጀርመን በዓመት 3,5% እድገት እንደሚያስገኝ ፣ በአንፃሩ፣ በአፍሪቃ ሀገራት ላይ የ3,5% ቅናሽ እንደሚያደርስ ነው ተንባዮች የገለጹት። በሚውንኽን የምጣኔ ምርምር ተቋም ባልደረባ ጋብርየል ፌልብማየር በአውሮጳ ህብረት እና በዩኤስ አሜሪካ መካከል ይፈረማል የሚባለው ስምምነት በተለይ በጥሬ አላባ የታደሉ እና በድርድሩ ተሳታፊ ያልሆኑትን አዳጊ ሀገራት በጠቅላላ ከምዕራቡ ገበያ እንዲገለሉ ወይም በነዚሁ ገበያዎች ውስጥ ሊሳተፉ የሚችሉበትን ሁኔታ አዳጋች ሊያደርገው እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ኬንያዊው የምጣኔ ሀብት ተመራማሪ ዴቪድ ኦኒሮ ውሉ የተቀረውንም ዓለም የሚነካ በመሆኑ የአውሮጳ ህብረት እና ዩኤስ አሜሪካ ስለ ንግድ ግንኙነታቸው እየተነጋገሩበት ያለው ድርድር ሁሉንም በዓለም የንግድ ድርጅት ውስጥ የሚጠቃለሉ ሀገራትን የሚያሳትፍ ቢሆን መልካም እንደነበር በመግለጽ፣ የድርድሩን ሂደት ነቅፈዋል።

Logo Welthandelsorganisation

አርያም ተክሌ

ልደት አበበ