1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ምክርቤት እና የአፍሪቃ ቀንድን የተመለከተወ ውይይት

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 19 2002

የአውሮጳ ምክር ቤት በአፍሪቃ ቀንድ በሚታዩት የፖለቲካ ችግሮች ላይ ትናንት በብራስልስ ውይይት አካሄደ።

https://p.dw.com/p/N82P
ምስል DW

የአፍሪቃ ቀንድ ፈተናዎች በሚል ርዕስ ስር የተካወያየውን ስብሰባ የጠራው በአውሮጳ ምክር ቤት የሚወከሉት ሶሻሊስት ፓርቲዎች ቡድን ነበር። ስብሰባውን የተከታተለው ወኪላችን ገበያው ንጉሴ እንደዘገበው፡ የስብሰባው ዓላማ በአፍሪቃው ቀንድ የሚታዩትን አሳሳቢ ችግሮች ስፋትና ጥልቀት ለማስገንዘብ ነው። በስብሰባው ከአውሮጳ ህብረት እና ከተለያዩ ተቋሞች የተጋበዙ ባለሙያዎች ተገኝተዋል። ነዋሪነታቸው በዩኤስ አሜሪካ የሆኑት የግንቦት ሰባት የፍትህ፡ የዴሞክራሲ እና የነጻነት ንቅናቄ ፕሬዚደንት ዶክተር ብርሀኑ ነጋም በዋና ተወያይነት ተጋብዘው ነበር።


ገበያው ንጉሴ
አርያም ተክሌ
ተክሌ የኋላ