1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ኅብረት ካውንስል ፕሬዚዳንት

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 29 2008

ኔዘርላንድስ ካለፈው ዓርብ ማለትም ከጎርጎሪዮሱ አዲስ ዓመት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ እስከሚቀጥለው ሰኔ 30፤ 2016 ዓመት ድረስ የአውሮጳ ኅብረት ካውንስል ፕሬዚዳንትነት ሥልጣንን ተረክባለች።

https://p.dw.com/p/1HaTW
Niederlande EU Ratspräsidentschaft Gruppenfoto mit dem König Willem Alexander
ምስል picture-alliance/AP Photo/P. Dejong

[No title]

የፕሬዚዳንትነት ሥልጣኑን ተረክባ ሥራዋን በይፋ ለመጀመሯም ትናንት በኔዘርላንድስ መዲና አምስተርዳም የአውሮጳ ኅብረት ባለሥልጣናት በተሳተፉበት ስብሰባ እና ስነ ሥርዓት ተበስሯል። የአውሮጳ ኅብረት ካውንስል ፕሬዚዳንትነት ሥልጣን ለአባል ሃገራት በየ ስድስት ወራት በዙር የሚደርስ ነው። ኔዘርላንድስ እስካሁን ለ12 ጊዜያት የፕሬዚዳንትነት ሥልጣን ደርሷታል። ይኽ የአሁኑ ሥልጣን ከ2004 ወዲህ የመጀመሪያው መሆኑ ተገልጧል። ኔዘርላንድስ የኅብረቱን ካውንስል በመምራቱ ሒደት ከፊቷ በርካታ ተግዳሮቶች መጋረጣቸውን የብራስልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሤ የላከልን ቀጣዩን ዘገባ ያብራራል።

ገበያው ንጉሤ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ